231
የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ ቻለው አመልካች ሐምሌ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው የሰበር አቤቱታ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ 284716 ሠኔ 19 ቀን 2012 አመልካች የተከሰሰነት የወንጀል ሕግ ከ15 ዓመት እስከ 25 ዓመት ፅኑ እሥራት የሚያስቀጣ በመሆኑ በዋስ ቢወጣ ወንጀሉ ከሚያስከትለው ቅጣት ሙሉ በሙሉ እንደማይቀርብ ፍ/ቤቱ ግምት ስለወሰደ የዋስትና መብቱ ወንጀሉ ከሚያስከትለው ቅጣት ሙሉ በሙሉ እንደማይቀርብ ፍ/ቤቱ ግምት ስለወሰደ የዋስትና መብቱ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 67/ሀ መሠረት ተነፍጓል በማለት የሰጠው ትዕዛዝ፣ይህንኑ ትዕዛዝ በማፅናት የፌደራል ደፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ 255442 ሐምሌ 21 ቀን 2012 ዓ.ም ሰጠው ፍርድ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሊታረም ገባል በማለት አቤቱታ በማቅረቡ ነው::
166
ኢትዮጵያዊ እናት እና አባት የሆኑት 1ኛ እና 2ኛ አመልካቶች በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት አሜቲካዊ የሆኒት የ2ኛ አመልካች እህት 3ኛ አመልካች የ1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች ልክ የሆነችውን ተማሪ ኤፍራታ ወንደሰን ቤተሰብ የሚያደርገውን ሁሉ ከልጅነቷ ጀምሮ ካለችበት ሀገር ሆና ስትንከባከባት የነበረች እና በምትኖርበት ሀገርም ልጇ መሆኗን የተለያዩ ፈርሞችን መሙላቷን አንስተው በአመልካቾች መካከል ተደረገው የተማሪ ኤፍራታ ወንደሰን የጉዲፈቻ ስምምነት እንዲፀድቅላቸው ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርበው ፍርድ ቤቱ በመዝገብ ቁጥር 103957 በ2/11/2011 በዋለው ችሎት የውጭ ሀገር ጉዲፈቻ በአዋጅ ቁጥር 103957 የተከለከለ ነው በማለት አቤቱታውን ባለመቀበል ትዕዛዝ ሰጥቷል ፡፡
171
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዳይ በሃዋላ የተላከ ገንዘብ ባንኩ ለማይገባ ሰው ከፍሏል በሚል ባንኪ ሃላፊ መደረጉን የሚመለከት ነው፡፡ክርክሩ የተጀመረው በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ፣የአሁኑ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡መዝገቡ የሚያሳየው የተጠሪ የክስ ምክንያት እ.ኤ.አ በ10/12/2018 ወይም እ.ኢ.አ በ 10/04/2011 ዓ.ም ከሊባኖስ ሀገር እህቱ በአሰሪዋ በአቶ ኤልያስ ኢልሀበር አማካኝነት በዌስተርን ዩኒየን ገንዘብ መላኪያ አማካኝነት 765 የአሜሪካን ዶላር ወይም በወቅቱ ምንዛሪ ብር
146
ጉዳዩ የጉዳት ካሳን መነሻ ያደረገ ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁን አመልካች 2ኛ ተከሳሽ ሲሆን 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ እንዲሁም 2ኛ ተጠሪ 1ኛ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ ከክርክሩ እንደተረዳነዉ 1ኛ ተጠሪ በአመልካች እና በ2ኛ ተጠሪ ላይ በመሰረተዉ ክስ 1ኛ ተጠሪ በቀን 24/07/2009 ዓ/ም ጠዋት 3፡00 ሰዓት በኦሮሚያ ክልል አስቦት በተባለ አካባቢ አሰሪዉ ስተን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር የአሁን አመልካችን የነዳጅ ማደያ ሲሰራ የዚህ ማህበር ሰራተኛ በመሆን እየገነባ ሳለ በአሁን 2ኛ ተጠሪ የተዘረጋ ከባድ የኤሌክትሪክ ሀይል ማስተላለፊያ ገመድ
171
ይህ ወራሽ የሌለዉ የዉርስ አክስዮን ድርሻ ክርክር የተጀመረዉ በፌዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪዎች የሥር ተከሳሾች ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የፌዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ.ቁ.167717 ግንቦት 30 ቀን 2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልን በማለት በማመልከቱ ነዉ።