በረቂቅ የስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ የአስተዳደር ሰራተኞች ግብአት የሚሰጡበት ሁኔታ መመቻቸቱ  ሰራተኞች በፍርድ ቤቶች የማሻሻያ ስራዎች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ እንዲሚያሰፋው ተገለጸ፡፡
/ Categories: News

በረቂቅ የስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ የአስተዳደር ሰራተኞች ግብአት የሚሰጡበት ሁኔታ መመቻቸቱ ሰራተኞች በፍርድ ቤቶች የማሻሻያ ስራዎች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ እንዲሚያሰፋው ተገለጸ፡፡

ከፌዴራል ፍርድ ቤቶች የተውጣጡ የአስተዳደር ሰራተኞች በአማካሪ ድርጅቱ በመዘጋጀት ላይ ባለው ረቂቅ የስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ተጨማሪ ግብአት እንዲሰጡ ሁኔታዎች መመቻቸታቸው የአስተደደር ሰራተኞች በፍርድ ቤቶች በመተግበር ላይ ባለው የማሻሻያ ስራዎች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ እንደሚያሰፋ ገለጹ፡፡

 

የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች ይህን የገለጹት በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሶስተኛውን የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ስትራቴጂክ ዕቅድ እንዲያዘጋጅ በተቀጠረው አድቫንስድ አሶሺየትስ እና አፕፍሮንት ጥምር አማካሪ ድርጅት በተዘጋጀ ረቂቅ ዕቅድ ገንቦት 27 ቀን 2013 ዓ.ም አስተያየት እንዲሰጡ በተዘጋጀ ወርክሾ ላይ ነው፡፡    

 

ሂደቱን እንዲከታተሉና ለአማካሪ ድርጅቱ ተቋማዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ በተቋቋሙ ዓብይና ቴክኒክ ኮሚቴ አማካኝነት የተዘጋጀው ይኸው ወርክ ሾፕ በዕቅድ ትግብራ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው የአስተዳደር ሰራተኞች በዕቅድ ዝግጅቱም ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በመጠቆም ረቂቁን በማዳበር አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ያለመ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሰራኞች የቅድመ ትግበራ ግንዛቤ እንዲያዳብሩ አስፈላጊነቱ የታመነበር በመሆኑ ነው፡፡ 

 

በወርክሾፑ አማካሪ ድርጅቱ ረቂቅ ስትራቴጂክ ዕቅዱን ለማዘጋጀት መሰረት የሆኑትን የሁኔታዎች ጥናትና ትንተና ስራዎች፤ ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊ ቴከኖሎጂያዊ እና አካባቢያዊ ተጽዕኖ ዳሰሳ እንዲሁም የጥንካዴ፣ ድክመት፣ መልካም አጋጣሚና ስጋት (ጥድመስ) ትንተናዎችን ግኝት የሚያብራራ ገለጻ ተቀርቧል፡፡ 

 

በተጨማሪም የረቂቅ ስትራቴጂክ ዕቅዱ ዋና ዋና ይዘቶች ማለትም ራዕይ፤ ተልዕኮ እና ዕሴቶች፤ ቁልፍ የትኩረት መስኮች፤ ግቦች እና ውጤት አመላካቾች ሰፊ ገለጻ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

 

ከሶስቱም ፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማለትም ከፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ፣ ከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች የተውጣጡት ተሳታፊዎች በግኝቶቹ እና በረቂቅ ዕቅዱ ላይ ያሏቸውን ጥያቄዎችና ተጨማሪ ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች አቅርበዋል፡፡ በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ የአብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት በክቡር አቶ ተኽሊት ይመስል የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ምክትል ፕሬዝደንት እና የአማካሪ ድርጅቱ ዕቅድ ዝግጅት ቡድን አባላት ማብራሪያ ተሰጥተዋል፡፡

 

በመጨረሻም ተሳታፊዎች የስትራቴጂክ ዕቅዱ የመጀመሪያ ክፍል የሆነው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ራዕይ፤ ተልዕኮ እና እሴቶች ላይ ያላቸውን አማራጭ በየፍርድ ቤቱ ስትራቴጂክ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል፡፡

 

በመረቀቅ ሂደት ላይ ያለው ሶስተኛው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ከመጨው ሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም ድረስ ለአምስት ተከታታይ ዓመታት የሚተገበር ይሆናል ተብሏል፡፡

 

የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Previous Article የፌደራል ፍርድ ቤቶች የአስተዳደር ሠራተኞች ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብ በቅርቡ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ይላካል
Next Article በፍትሃ ብሔር ፍርደ አፋጻጸም በሚታዩ ተግዳሮቶች እና ሊወሰዱ በሚገባቸው የማስትካከያ እርምጃዎች ላይ ምክክር ተደረገ
Print
123