መግቢያ
Next Topic 

ይህ ሲስተም በድረ ገፅ አድራሻ http://www.fsc.gov.et የሚሮጥ የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን በተመለከተ የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጥ ድረ ገፅን መሰረት ያደረገ ሲስተም (Web based application) ነው። ይህ ሲስተም የሚሰጠው አገልግሎት ዘርፈ ብዙ ሲሆን የሲስተሙ ዓይነተኛ ዓላማ የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን አሠራር ዘመናዊ፥ ቀልጣፋ፥ ግልጽና በቀላሉ ተደራሽ ማድረግ፤ ማህበረሰቡ በፍትህ ዙሪያ ያለውን ንቃት ማጎልበት፤ የፍትህ አሰጣጥ ሥርዓቱን ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሆን ማገዝ የመሳሰሉት ተጠቃሾች ናቸው። ይህ ሲስተም ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መሃከል ከብዙ በጥቂቱ፦

ይህ ሲስተም ከላይ የተጠቀሡትንና ሌሎች ተጨማሪ አገልግሎቶችን ለመስጠት ወደ አገልግሎቱ የሚያመሩ የተለያዩ ሊንኮች አካቷል። እነዚህም ሊንኮች በሁሉም የድረ ገፁ ገፆች በአራት አቅጣጫ ይገኛሉ።

ባጠቃላይ የፌዴራል ፍርድ ቤት የድረ ገፅ ሊንኮቹን በአራት ዋና ዋና ክፍል በመክፈል ተገልጋዮች የሚከናውኑትን ክንውን ከሊንኮቹ አንፃር መመልከት ይቻላል። እነዚህም ሊንኮች በሥራቸው ተጨማሪ ሊንኮችን ሊይዙ የሚችሉ ሲሆን፤ እነርሱም፦

የድረ ገፁ የላይኛው ሊንኮች

የድረ ገፁ የበስተግራ ሊንኮች

የድረ ገፁ የበስተቀኝ ሊንኮች

የድረ ገፁ የግርጌ ሊንኮች 

ይህ የአጠቃቀም መመሪያ የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን ድረ ገፅ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ለማስረዳት የተዘጋጀ ነው። በዚህም መሰረት ይህ የአጠቃቀም መመሪያ የተከፋፈለው በነዚህ ሊንኮች ሲሆን፤ እነዚህን ሊንኮች በመጠቀም በሚመጡ ገፆች ውስጥ የሚገኘውን አገልግሎት እንዲሁም በሚመጡት ገፆች ውስጥ የሚገኙትን ተጨማሪና የተለዩ ሊንኮች አገልግሎት ጨምሮ ያብራራል። በዚህ የአጠቃቀም መመሪያ እነዚህን ሊንኮች ዋና ሊንኮች በመባል ይገለጻሉ።

ይህ ሲስተም በአራት ቋንቋዎች ማለትም አማርኛ፣ English Oromiffa እና ትግርኛ አገልግሎት እንዲሰጥ ታልሞ የተሠራ ነው። ይህም በመሆኑ ተጠቃሚው በሲስተሙ ለመጠቀም የሚፈልግበትን ቋንቋ በሚቀይርበት ጊዜ የሚቀየረው ቋንቋ የድረ ገፁ ሊንኮች እና የድረ ገፁ መልዕክቶች ብቻ ናቸው። የድረ ገፁ ሌሎቹ መረጃዎች በሙሉ በአማርኛ ይሆናሉ። የዚህም ዋናው ምክንያቱ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የስራ ቋንቋ አማርኛ ስለሆነ እና መረጃዎቹ ዳታቤዝ (Database) ውስጥ የተቀመጡት በአማርኛ በመሆኑ ነው። ይህ ሲስተም ሲጀምር በአማርኛ ቋንቋ የሚጀምር በመሆኑ ይህ የአጠቃቀም መመሪያ የተዘጋጀው አማርኛ ቋንቋን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ነው።

ይህንን ሲስተም ለማስጀመር በድረ ገፅ አድራሻ http://www.fsc.gov.et መጠቀም ያስፈልጋል። በዚህን ጊዜ ቀጥሎ በሥዕሉ የሚታየው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የመጀመሪያ ገፅ ይመጣል።

ሥዕል 1 የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የመጀመሪያ ገፅ

ከዚህ ቀጥሎ ባሉት የዚህ መመሪያው ክፍሎች የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ተጠቃሚዎች ከድረ ገፁ ሊንኮች አንፃር የሚያከናውኗቸው ተግባሮች የሚያስቃኝ ይሆናሉ።

ማስታወሻ፦