ወ/ሮ ማስተዋል መኩሪያ እና የቤኒሻንጉል...

ቅሬታውም  የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡የስልጣን ጉዳይ የሚመነጨው ከህግ እንጂ ከሌላ ስላልሆነ በህግ በግልጽ ያልተሰጠውን... Read more

አቶ መላኩ ካሳዉ ዓለሙ እና የኢትዮጵያ...

ጉዳዩ የሥራ ክርክር ሲሆን አመልካችም በተጠሪ መስሪያ ቤት ዉስጥ ከ1980 ዓ.ም ጀምሮ በተለያየ የሥራ መደብ ላይ ሲሠሩ ቆይተዉ ነሐሴ 01 ቀን 2014 ዓ.ም ጡረታ በመዉጣታቸዉ የስራ ዉላቸዉ መቋረጡንና በወቅቱም ደመወዛቸዉ ብር... Read more

አቶ ካሳሁን ወረዳ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ...

ጉዳዩ የአመት እረፍት በገንዘብ ተቀይሮ እንዲከፈለኝና የምስክር ወረቀት እንዲሰጥኝ ክርክርነ የተመለከተ ሲሆን አመልካችም የሥር ፍ/ቤቶች የአሁን አመልካች ያልተጠቀምኩባቸዉ የ2012 ዓ.ም፣ የ2013 ዓ.ም እና የ2014 ዓ.ም... Read more

ወ/ሮ አስያ ሐጂ አብዲ እና እነ አቶ...

ጉዳዩ የባልና ሚስት ክርክርን የሚመለከት ሆኖ አቤቱታውም ለክርክሩ መነሻ የሆኑት ከብቶች እና ይዞታ በጋብቻ ጊዜ በሽሪያ ፍ/ቤት በኒካ የተቆጠሩ ስለመሆኑ በስር ፍ/ቤት በማስረጃ ተረጋግጦ እያለ አዲስ ጭብጥ በመመስረት ጋብቻ ሲፈጸም... Read more
1345678910Last
«September 2023»
MonTueWedThuFriSatSun
28293031123
45678910
11121314151617
18192021222324
2526272829301
2345678

በሽግግር ፍትሕ ሂደት የዳኞች ሚና በሚል ርዕስ ሀገራዊ...

66

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከኢጋድ ጋር በመሆን ለሶስት ቀናት በሽግግር ፍትሕ የዳኞች ሚና በሚል ርዕስ በቢሾፍቱ ከተማ ሲካሄድ የቆየው ወርክሾፕ ተጠናቀቀ፡፡

ወርክሾፑን በንግግር የከፈቱት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ እንደገለጹት ዳኞች አድካሚ የዳኝነት ስራ አጠናቀው በሚገኙበት በአሁኑ የእረፍት ጊዜ የዳኞችን አቅም ለማገንባት የሚያስችል፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ትኩረት በተሰጠው የሽግግር ፍትሕ ጉዳይ ላይ ወርክሾፕ መዘጋጀቱ በቀጣይ የሚቀርቡ የሽግግር ፍትሕ ጉዳዮች ላይ በቂ ግንዛቤ እና እወቀት በመያዝ ለመስራት የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት...

132

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አዲስ ለሚያሰራው የህጻናት ማቆያ የሚሆን ግምታቸው ብር 35,000 (ሰላሳ አምስት ሺህ) ብር የሚያወጡ የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ፡፡

ዜና መግለጫ

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 30/2016 ዓ.ም ድረስ በከፊል ዝግ ይሆናሉ፡፡

107

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በሕገ መንግስቱ እና በሕግ በተሰጣቸው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት የሚቀርቡ ጉዳዮችን በማስተናገድ የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን፣ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲጠበቁ ሰላም እና ስርዓት እንዲከበር የማድረግ ተግባራትን እየተወጡ ይገኛሉ፡፡

በዚህ መሰረት በ2015 በጀት ዓመት በነበረዉ የመዛግብት አፈጻጻም አንጻር ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች በአጠቃላይ 213,116 መዛግብት ቀርበዋል። ከእነዚህም ዉስጥ ለ184,467 (86.56%) መዛግብት እልባት መስጠት የተቻለ ሲሆን 28,675 (13.44%) መዛግብት ደግሞ ወደ 2016 በጀት ዓመት ተሻግረዋል፡፡ የበጀት ዓመቱ አፈጻጸም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ2014 በጀት ዓመት ለፌ/ፍ/ቤቶች የቀረቡት 209,317 መዛግብት ሲሆኑ ዕልባት ያገኙት ደግሞ 176,767 ነበሩ፡፡ በዚህም መሠረት በ2015 በጀት ዓመት የቀረቡት መዛግብት በ2014 በጀት ዓመት ከቀረቡት በ3,799 (1.8%) ከፍ ያሉ ሲሆን በተመሳሳይ ዕልባት ያገኙትም በ7,670 (4.3%) መዛግብት ከፍ ያሉ ናቸው፡፡

የፍርድ ቤቶቹ አፈጻጸም በተናጠል ሲታይ ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት 26,185 መዛግብት ቀርበው ለ19,201 ዕልባት የተሰጠ ሲሆን 6,984 መዛግብት ወደ 2016 በጀት ዓመት ተሻግረዋል፡፡ በተመሳሳይ በ2015 በጀት ዓመት ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡት የመዛግብት ብዛት 33,721 ሲሆን 26,301 መዛግብት ዕልባት አግኝተዋል፡፡ ወደ 2016 የተሻገሩት መዛግብት ብዛትም 7,420 ሆኗል፡፡ እንዲሁም ለፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት የቀረቡት 153,210 መዛግብት ሲሆኑ 138,965 ዕልባት በማግኘታቸው 14,245 ወደ 2016 በጀት ዓመት ተላልፈዋል፡፡

የፌደራል ፍርድ ቤቶች አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ...

164

(ሐምሌ 15/2015 ዓ.ም፣) የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክቡራን ፕሬዚዳንቶች ፣ ክቡራን ዳኞች እና የሥራ ኃላፊዎች የተሳተፉበት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐግብር በአዲስ አበባ ጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ሐምሌ 15 ቀን 2015 ዓ.ም ተከናወነ፡፡

1345678910Last

/ Categories: Auction

ሀራጅ ማስታወቂያ

ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት

Previous Article የሀራጅ ማስታወቂያ
Print
6248

Documents to download