Selam Warga / Wednesday, June 26, 2024 / Categories: News, CJPO NEWS በህጻናት ዝቅተኛ የወንጀል ተጠያቂነት እድሜ ላይ ያተኮረ ስልጠና እና ውይይት ከኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር ተካሄደ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት እና በUNFPA ትብብር የህጻናት የወንጀል ተጠያቂነት ዝቅተኛ እድሜን በተመለከተ ሰኔ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከክቡራን የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ውይይት ተደርጓል የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሕፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዳኛ ተክለሐይማኖት ዳኜ የስልጠና እና ውይይት መድረኩ የተዘጋጀበትን ዓላማ ሲገልፁ በአገራችን ያለው ዝቅተኛ የወንጀል ተጠያቂነት እድሜ 9 ዓመት መሆኑን አስታውሰው ይህ ከህጻናቱ መብት እና ጥቅም፣ ከዓለም አቀፍ ህጎች እንዲሁም ከአገራት ተሞክሮዎች አንጻር መዳሰስ በማስፈለጉ መሆኑን አመላክተዋል ለውይይቱ መነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት ዶክተር ዮናስ ቢርመታ የወንጀል ተጠያቂነት ዝቅተኛ እድሜ አወሳሰን መርህ፣ ህጎች እና ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እንዲሁም የሀገራችን ሁኔታ ላይ ገለጻ አቅርበዋል፡፡ በመቀጠልም የጉዳዩን እይታ ከዳኝነት እና ችሎት ነባራዊ ሁኔታ አንጻር ዳኛ ልዑለስላሴ ሊበን እንዲሁም ከህጻናት እድገት እና ኃላፊነት መቀበል አንጻር ዶክተር እመቤት ሙሉጌታ ማብራሪያ ሰጥተዋል በስልጠና እና ውይይቱ ላይ ክቡራን የቋሚ ኮሚቴ አባላት ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን በመጨረሻም የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ ውይይቱ ጠቃሚ መሆኑን አንስተው በጉዳዩ ላይ የአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ የአገራትን ተሞክሮ በመውሰድ በዘርፉ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት የሚረዱ ጥናቶች መከናወን እንዳለባቸው እና ለዚህም ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት የሚፈለግባቸውን እንዲሰሩ አሳስበዋል Previous Article በረቂቅ የህፃናት ፍትህ የስልጠና ሞጁል ላይ የግብአት ማሰባሰቢያ ዉይይት ተደረገ Next Article የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአፍሪካ ህብረት በህጻናት ጥበቃ ጉዳዮች እና ሌሎች ጎጂ ተግባራት በኢትዮጵያ ሀገራዊ የክትትል ተልዕኮ ወርክሾፕ ላይ በመገኘት ሪፖርት አቀረበ Print 531