Selam Warga / Monday, December 9, 2024 / Categories: News, CJPO NEWS በተባበሩት መንግስታት የህጻናት መብቶች ኮሚቴ አማካኝነት እየተዘጋጀ ባለው General Comment 27 on Access to Justice for children ላይ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት ተካሄደ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናትና ፍትህ ፕሮጀክት በተባበሩት መንግስታት የህጻናት መብቶች ኮሚቴ አማካኝነት እየተዘጋጀ ባለው General Comment 27 on Access to Justice for children የሃገራችን ህጻናት አስተያየት ለማካተት በማሰብ ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከአዲስ አበባ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች እና የህጻናት ፓርላማ የተውጣጡ ህጻናትን በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በማሰባሰብ ግብዓት ተቀብሏል፡፡ በዕለቱም ህጻናት በፍትህ ስርዓት ውስጥ በሚያልፉባቸው በወንጀል ተጠቂ ወይም ምስክር በመሆን፣በወንጀል ነክ ጉዳይ ውስጥ በመግባት ወይም በተለያዩ የፍ/ብሄር ክርክሮች ውስጥ ፍትህ ሲያገኙ ምን ምን ፍላጉት እንዳሏቸው ፤ ምን ምን ተግዳሮቶች እንደሚገጥማቸው እና ምን ቢደረግ ፍርድ ቤቶችን ለህጻናት ተስማሚ ማድረግ እንደሚቻል በህጻናት ፍትህ ዳይሬክቶሬት ውስጥ የፕሮጀክት ባለሙያ በሆኑት አቶ ዮሃንስ ፍቃዱ ገለጻ ተደርጓል፡፡ ህጻናቱም ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ለውይይቱ ግብዓት የሚሆን መረጃን በቃልና በጽሁፍ ሰጥተዋል ፡፡የተሰበሰበው ግብዓት ተሰናድቶ በቀጥታ ለተባበሩት መንግስታት የህጻናት መብቶች ኮሚቴ የሚላክ ሲሆን በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ህጻናቱ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስማርት ኮርት ሩሞች/ችሎት አዳራሽ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ Previous Article ፍርድ ቤቱ የህጻናት ቀለብ አወሳሰን መምሪያና የዳኞች ለህጻናት ተስማሚ ፍትህ የስልጠና ማንዋልን አስመረቀ Print 168