Selam Warga / Tuesday, January 13, 2026 / Categories: News የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እጩ ዳኞችን ሹመት አጸደቀ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታህሳስ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደዉ 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባ በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 81(2) መሰረት 34 የከፍተኛ ፍርድ ቤት እጩ ዳኞችን ሹመት አጽድቋል፡፡ ክቡራን ዳኞቹ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ከፍርድ ቤቱ ፕሬዝንደት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፣ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ ሌሊሴ ደሳለኝ እንዲሁም የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉበኤ ጽ/ቤት ሃላፊ ክቡር ዳኛ ቡላ ዋጋሪ ጋር ትውውቅ ከማድረግ በተጨማሪ የስራ አቅጣጫ ተሰጥቷል። የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለተሿሚ ዳኞች መልካም የስራ ግዜን ይመኛል። Print 187