Welcome to Child Justice Project Directorate


የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ሲያደርጉ የነበረው ጉብኝት እና ውይይት ተጠናቀቀ
Selam Warga
/ Categories: News

የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ሲያደርጉ የነበረው ጉብኝት እና ውይይት ተጠናቀቀ

የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት ከቀን 21/04/2018 ዓ.ም እስከ 27/04/2018 ዓ.ም ለተከታታይ 5 የስራ ቀናት ጉብኝት እና ውይይት አድርገዋል፡፡

በቆይታቸውም የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የተዘረጉ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች እና የለሙ የተለያዩ መተግበሪያዎች ምልከታ ያደረጉ ሲሆን ከፍርድ ቤቱ አመራሮች እና ከሚመለከታቸው ባለሙያዎች ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ክቡራን ዳኞቹም ባደረጉት ምልከታ እየተሰሩ ላሉ የቴክኖሎጂ ሪፎርሞች ያላቸውን አድናቆት በመግለጽ ቴክኖሎጂዎችን በተመለከተ ሀሳብ አስተያየቶችና ጥያቄዎችን በማንሳት ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡

ጉብኝቱ በትግበራ ወቅት በቀላሉ ወደ ስራ ለመግባት የሚያግዝ በመሆኑ መሰል ጉብኝቶች እና ውይይቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ተብሏል፡፡

Print
217