Welcome to Child Justice Project Directorate


የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአፍሪካ ህብረት በህጻናት ጥበቃ ጉዳዮች እና ሌሎች ጎጂ ተግባራት በኢትዮጵያ ሀገራዊ የክትትል ተልዕኮ  ወርክሾፕ ላይ በመገኘት ሪፖርት አቀረበ
Selam Warga
/ Categories: News, CJPO NEWS

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአፍሪካ ህብረት በህጻናት ጥበቃ ጉዳዮች እና ሌሎች ጎጂ ተግባራት በኢትዮጵያ ሀገራዊ የክትትል ተልዕኮ ወርክሾፕ ላይ በመገኘት ሪፖርት አቀረበ

ፍርድ ቤቱን በመወከል ገለጻ ያደረጉት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዳኛ ተክለሐይማኖት ዳኜ ሲሆኑ ፍርድ ቤቶች የህጻናትን መብት እና ጥቅም ትርጉም ባለው መልኩ ለማስጠበቅ እንዲረዳ መመሪያዎችን በማውጣት፣ለህጻናት ተስማሚ ፍርድ ቤቶችን በማደራጀት፣ነጻ የህግ እና ማህበራዊ ሳይንስ ድጋፍ በመስጠት፣የዳኞችን አቅም በማሳደግ፣አባትነትን በዘረ-መል ምርመራ በማረጋገጥ ፣ በወንጀል ነክ ጉዳይ ገብተው የተገኙ ህጻናት አገልግሎት በማሻሻል እንዲሁም ሌሎች ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ከዚህም ባለፈ የወርክሾፑ ተሳታፊዎች በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመገኘት የህጻናት የህግ ከለላ ማዕከልን እንዲሁም ለህጻናት ተስማሚ ችሎትን ጎብኝተዋል፡፡

Previous Article በህጻናት ዝቅተኛ የወንጀል ተጠያቂነት እድሜ ላይ ያተኮረ ስልጠና እና ውይይት ከኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር ተካሄደ
Next Article ፍርድ ቤቱ የህጻናት ቀለብ አወሳሰን መምሪያና የዳኞች ለህጻናት ተስማሚ ፍትህ የስልጠና ማንዋልን አስመረቀ
Print
590