Temesgen Alemayehu / Wednesday, August 9, 2023 / Categories: News, CJPO NEWS የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የህጻናት ማቆያ የሚሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አዲስ ለሚያሰራው የህጻናት ማቆያ የሚሆን ግምታቸው ብር 35,000 (ሰላሳ አምስት ሺህ) ብር የሚያወጡ የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ፡፡ በርክክብ ሥነሥርዓቱ ላይ የተገኙት የፍ/ቤቱ ምክትል ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ተክሊት ይመስል በፍ/ቤቱ የህጻናት ማቆያ አለመኖሩ የፍ/ቤቱ ሰራተኞች ስራቸውን ተረጋግተው እንዳይሰሩ እና ውጤታማ እንዳይሆኑ ከዚህም ባለፈ ስራቸውን ትተው ቤት እንዲቀመጡ ሲያደርግ የነበረ መሆኑን ገልጸው ይህ ድጋፍ መደረጉ ሰራተኞች ተረጋግተው ልጆቻቸውን በቅርበት እንዲንከባከቡ እና በስራቸውም ውጤታማ ስራ እንዲሰሩ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊ ዳኛ ተ/ሐይማኖት ዳኜ በበኩላቸው የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዋነኛ ዓላማው ፍ/ቤቶችን ለህጻናት ምቹ እንዲሆኑ ማስቻል በመሆኑ ድጋፉ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት Previous Article በቤተሰብ አስማሚነት ላይ የተዘጋጀ የሥልጠና እና የውይይት መድረክ ተካሔደ Next Article ወንጀል ነክ ነገር ዉስጥ ገብተዉ የተገኙ ወጣቶችና በሴቶችና ህጻናት ችሎት ያጋጠሙ መልካም ተሞክሮዎችና ተግዳሮቶች (Children in conflict with the law) በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ከፌደራልና ክልል ፍርድ ቤቶች ከተዉጣጡ ዳኞችና ማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡ Print 2290