17Nov2025 Read more በዲጂታል የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ በዋነኝነትም በኢንቲግሬትድ ኬዝ ማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተም (ICMIS) ሲስተም ላይ ከቀን 06-07/03/2018 ዓ.ም ለሁለት ቀናት ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ሲሰጥ የቆየው የተግባር ልምምድ (ስልጠና) ተጠናቀቀ ። በስልጠናው የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ድሪባ ፈዬራ ክቡራን ዳኞች ላደረጉት ንቁ ተሳትፎና በመድረኩ ለተነሱት ገንቢ ሀሳብ አስተያየቶች አመስግነው ቴክኖሎጂው በቅርቡ ወደ ትግበራ ስለሚገባ ለትግበራው ውጤታማነት ስልጠናው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
17Nov2025 Read more በአገልግሎት አሰጣጥና የደንበኞች አያያዝ ላይ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ የፌደራል የህግና የፍትሕ ኢንስቲትዩት ለተከታታይ ሦስት ሳምንታት በሶስት ዙር ከፌዴራል ፍርድ ቤቶች፣ከፍትሕ ሚኒስቴር እንዲሁም ከፌዴራል የሕግና የፍትሕ ኢንስቲትዩት ለተውጣጡ 170 የአስተዳደር ሰራተኞች ከጥቅምት 21 ቀን እስከ ህዳር 6ቀን 2018 ዓ.ም በፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል፡፡
17Nov2025 Read more የተግባር ልምምድ (ስልጠና) በዲጂታል የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች እየተሰጠ ይገኛል በዲጂታል የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከቀን 06-07/03/2018 ዓ.ም ለሁለት ቀናት የሚቆይ የተግባር ልምምድ (ስልጠና) ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች እየተሰጠ ይገኛል።
17Nov2025 Read more የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሪሶርስ ኢንሪቺንግ አፍሪካን ላይቭስ በሚባል ግብረ ሰናይ ድርጅት አስተባባሪነት የተሰበሰቡ መጽሃፍቶችን ተረከበ ሪሶርስ ኢንሪቺንግ አፍሪካን ላይቭስ በመባል የሚጠራ ግብረ ሰናይ ድርጅት ቡክስ ፎር አፍሪካና ቶምሰን ሪዉተርስ ከሚባሉ ለጋሽ ድርጅቶች ለትምህርት ቤቶች እና ለፍትህ ተቋማት የሚያገለግሉ መጻሃፍቶችን በማሰባሰብ ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ አድርጓል፡፡
7Nov2025 Read more በአስማሚነት ክህሎት ዙሪያ ሲሰጥ የነበረዉ የተግባር ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት ከጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ 4 ቀናት በተግባር ሲሰጥ የነበረዉ የአስማሚነት ክህሎት ስልጠና ተጠናቋል፡፡