Welcome to Child Justice Project Directorate


የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የሶማሊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቴክኖሎጂ ስራዎችን በይፋ አስጀመሩ Read more

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የሶማሊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቴክኖሎጂ ስራዎችን በይፋ አስጀመሩ

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የሶማሊ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቪድዮ ኮንፍረንስ፣በሶማሊኛ ቋንቋ የሚሰራ የመዝገብ አስተዳደር፣ የኢፋይሊንግ አገልግሎት እንዲሁም የቀጠሮ መከታተያ አገልግሎትን በቀን 12/02/2018 ዓ.ም የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ክቡራን ፕሬዝደንቶች ባሉበት በይፋ አስጀምረዋል፡፡

የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህንጻ እድሳትና የዲጂታላይዜሽን ስራዎች ምርቃት እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ እና መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት  ጉብኝት ተካሄደ Read more

የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህንጻ እድሳትና የዲጂታላይዜሽን ስራዎች ምርቃት እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ እና መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉብኝት ተካሄደ

የሀረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የድሬዳዋ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ እና መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የህንጻ እድሳትና የዲጂታላይዜሽን ስራዎች ምርቃት በቀን 11/02/2018 ዓ.ም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፣ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ የሀረሪ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ ሱልጣን አ/ሰላም እንዲሁም የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ክቡራን ፕሬዝደንቶች ባሉበት ተካሂዷል፡፡

በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ሲመክር የቆየው ሀገር አቀፍ የህግ ተርጓሚዎች መድረክ የጋራ አቋም በመያዝ ተጠናቋል፡፡ Read more

በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ሲመክር የቆየው ሀገር አቀፍ የህግ ተርጓሚዎች መድረክ የጋራ አቋም በመያዝ ተጠናቋል፡፡

ለሁሉም ፍርድ ቤቶች የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ በመወያየት የዳኞች ያለመከሰስ መብት በህገ- መንግስቱ ላይ በተቀመጠ መሰረት ተግባራዊ ባልተደረገባቸው ክልሎች የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር፣ሁሉም ፍርድ ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጣቸዉን እንዲያዘምኑ የሚያደርግ የቴክኖሎጂ መሰረት ልማትን የሚዘረጉበት በቂ በጀት እንዲያገኙ ሁሉም ትብብር እንዲያደርግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ እየተወያዩ መፍትሔ ለማምጣት የጋራ አቋም ተይዟል፡፡

ኒታ (National Institute for Trial Advocacy (NITA)) እና ጆንስ ዴይ (JONES DAY) የተባሉ መቀመጫቸውን አሜሪካን ሀገር ያደረጉ ግብረሰናይ ድርጅቶች ከፍተኛ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ልዑካን ቡድን በጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመገ Read more

ኒታ (National Institute for Trial Advocacy (NITA)) እና ጆንስ ዴይ (JONES DAY) የተባሉ መቀመጫቸውን አሜሪካን ሀገር ያደረጉ ግብረሰናይ ድርጅቶች ከፍተኛ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ልዑካን ቡድን በጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመገ

ልዑካን ቡድኑ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በሙግት አሰማም ሒደት (Trial advocacy) ላይ ለተከላካይ ጠበቆች ተግባር ተኮር ሥልጠና ለመስጠት ሲሆን ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በፍርድ ቤቱ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

18ኛው የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተከበረ Read more

18ኛው የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተከበረ

በአገር አቀፍ ደረጃ "ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ!" በሚል መሪ ቃል 18ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በተገኙበት ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል ሥነሥርዓት ተከብሯል፡፡

First45679111213Last