8Jun2026 Read more በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተሰሩ ያሉ የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ ለተቋሙ የቀድሞ አመራሮች ገለጻ ተደረገ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፕሬዝዳንትነትና ምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩ የቀድሞ አመራሮች በፍርድ ቤቱ ተገኝተው አሁን ላይ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ ውይይትና ምልከታ አድርገዋል።
28May2026 Read more ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል የስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት የተሰራ ዘመናዊ የህጻናት ማስመስከሪያ ክፍል (One way mirror) በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት በይፋ ስራ ጀምሯል።
25May2026 Read more ለሶሻል ወርክ ባለሞያዎች በተዘጋጀ የስልጠና ማንዋል ረቂቅ ላይ የቫሊዴሽን ወርክ ሾፕ ተካሄደ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት በፍትህ ስርዓት ውስጥ የሚያገለግሉ የማህበራዊ ሳይንስ ባለሞያዎችን ሚና ለማጎልበት የሚያግዝ የስልጠና ማንዋል የመጨረሻ ረቂቅ ሰነድ ላይ የውይይት እና የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሂዷል፡፡
21May2026 Read more የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተከናወኑ የሪፎርም እና የዲጂታላይዜሽን ሥራዎችን ጎበኙ በኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ እና የጄሲኢ (JCE) ሰብሳቢ በሆኑት በክብርት ዳኛ ሱዛን ኞኪ ንዱንጉ የተመራው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ላለፉት ሦስት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር አጠናቋል።
20May2026 Read more በመሰረታዊ የክስ መደራደር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ከፌዴራልና ከክልል ለተውጣጡ የዳኝነትና የፍትህ አካላት አመራሮች፣ ዳኞች እንዲሁም የሕግ ባለሙያዎች በመሰረታዊ የክስ መደራደር ( Plea bargaining) ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከፔፐርዳይን ዩኒቨርሲቲ በተጋበዙ አሰልጣኞች ተሰጥቷል።