ጉዳዩ የስራ ክርክር ሲሆን በተጀመረበት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡
ተጠሪ በ08/11/2011 ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት ክስ በአመልካች ሆቴል ውስጥ በዋና ምግብ አዘጋጅነት የስራ መደብ በወር ብር 85,554 እየተከፈለኝ ስሰራ ቆይቼ ግንቦት 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ በግንቦት 14 ቀን 2011 ዓ.ም. በነበረው የሙስሊሞች ጾም አፍጥር ዝግጅት ላይ ጉድለት አሳይተሀል በሚል ከግንቦት 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ የስራ ውሌን አቋርጧል፡፡ ነገር ግን የፈጸምኩት ጉድለት የለም፡፡ ጉድለት አለ ቢባል እንኳን ያለማስጠንቀቂያ ከስራ የሚያሰናብት ባለመሆኑ ስንብቱ ህገወጥ ነው ተብሎ አመልካች የማስጠንቀቂያ ጊዜ፤ የካሳ እና የስንብት ክፍያ እንዲሁም የአንድ ወር ደመወዝ በድምሩ ብር 705,820 እንዲከፍል ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡…………..