መሀመድ አባ ቡልጉ እና የጌምቤ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የሰ.መ.ቁ 198400
ጉዳዩ የይዞታ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጅማ ዞን ጎማ ወረዳ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በሥር ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር የአሁን አመልካች ከሳሽ፤ የአሁን ተጠሪ ተከሳሽ፤ በዚህ የሰበር ክርክር የሌለው የጌምቤ ከተማ መምሕራን ማህበር እነ አቶ ደሳለኝ አበበ / 14 ሰዎች ደግሞ ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ የአሁን አመልካች በሥር ፍ/ቤት ያቀረበው ክስ ይዘት በአጭሩ፡- አመልካች በሕጋዊ መንገድ የያዝኩት አንድ ፈጫሳ የቡና ችግኝ እና አንድ ፈጫሳ ባህር ዛፍ በ 2004 ዓ.ም ተክለው ጸድቆ የነበረ መሆኑን፤ ተጠሪ ምንም ካሳ ሳይሰጣቸው ከአመልካች ወስዶ ለሰዎች ሲሰጥ የቀረውን አንድ ፈጫሳ በጌምቤ ከተማ ከሶ በር አካባቢ ተብሎ በሚጠራው አዋሳኙ በክሱ ላይ በተገለጸው ይዞታ ውስጥ በቀን 23/09/2011 ዓ.ም በመግባት አጠቃላይ ግምቱ ብር 3830 የሚያወጣ አራት ደጃፍ 3*4 የሆነ 10 ቅጠል ቆርቆሮ ቤት፤ መሪ እንጨት እና ማገር እንዲሁም ከንች ያፈረሰባቸው መሆኑን በመግለጽ አፍርሶ የወሰደውን የንብረት ግምት ብር 3830 / ሶስት ሺሕ ስምንት መቶ ሠላሳ ብር / እንዲከፍላቸው እና በይዞታቸው ላይ የፈጠረው ሁከት እንዲወገድ ይወሰንላቸው ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡………..
7034
Documents to download
-
198400(.pdf, 831.77 KB) - 687 download(s)