ቻይና ዊ ዩ ኮ (ሊሚትድ) የኢትዮያ ቅርንጫፍ እና አቶ ሞገስ አለሙ የሰ/መ/ቁጥር.221229
ጉዳዩ የጉዳት ካሳ ሃላፊነት የሚመለከት ሲሆን በስር ፍርድ ቤት ከሳሽ ተጠሪ ሲሆን አመልካች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡የክሱ ይዘት ባጭሩ አመልካች ከአሸሬ ዙፋን አንገረብ ፕሮጀክት መንገድ አስፋልት ለመገንባት ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በዉል የተረከበዉን መንገድ ሲገነባ የተጠሪ ይዞታ የሆነ አንድ ተኩል ሄክታር መሬት ላይ ከግንባታዉ የሚያወጣዉን አላስፈላጊ ቋጥኝ እና አፈር ማስወገጃ በማድረግ መሬቱ ለዘለቀታዉ ሰብል ማምረት እንዳይችል አድርጎብኛል፡፡ከዚህ የእርሻ መሬት በአመት አስር ኩንታል ሰሊጥ ምርት አገኛለሁ፤የአንድ ኩንታል ዋጋ ብር አምስት ሺህ ሲሆን በኣመት ብር ሃምሳ ሺህ ሁኖ የአስር ዓመት ብር አምስት መቶ ሺህ (500,000) ነዉ፡፡ይህንኑ የጉዳት ካሳ እንዲከፍል እንዲሰወን በማለት ዳኝነት የጠየቀ ሲሆን አመልካች በኩል ባቀረበዉ መልስ ይዞታነቱ የተጠሪ የሆነውን ቦታ ለአፈር መድፊያነት ለመጠቀም በ2010ዓ.ም መከራየቱን፤በወቅቱ ለአንድ ዓመት ብር አስር ሺህ መክፈሉን፤በ2011ዓ.ም የኪራይ ዉሉ ባለመታደሱ ተጠሪ በማእካለዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ አቅርቦ ብር ሰማኒያ ሺህ መክፈሉን እስከ ሚያዝያ 30 2012ዓ.ም ለመጠቀም ተስማመምቶ ጉዳዩ በእርቅ መቋጨቱን እና በተጠቀሰዉ ጊዜ ዉስጥ ስራ ባለመጀመሩ ቦታዉን አለመጠቀሙን እንዲሁም የተጠቀመዉ መሬት ሩቡን ብቻ ስለመሆኑና በዉሉ መሰረት ይህንኑ አስተካከሎ ማስረከብ እንጂ ካሳ የመክፈል ግዴታ የሌለበት መሆኑን ጠቅሶ ክሱ ዉድቅ እንዲደረግ መከራከሩን መዝገቡ ያሣያል፡፡መልካም ንባብ…….
920
Documents to download
-
221229(.pdf, 845.32 KB) - 144 download(s)