ነጋቲ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና አበራሽ በየነ የሰ/መ/ቁጥር 228917
ጉዳዩ የስራ ክርክር ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን አሠሪ እና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ አመልካች ተከሳሽ ተጠሪዎች ደግሞ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡
ተጠሪዎች በመስከረም 26 ቀን 2014 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የስራ መደቦች በተለያየ ጊዜ ተቀጥረን ስንሰራ የቆየን ቢሆንም የሠራተኛ ማህበር መስርታችኋላ እና የምትሰሩት ምርት በገበያ ላይ ተፈላጊ አልሆነም በሚሉ ምክንያቶች በመጋቢት 25 ቀን 2013 ዓ.ም በተጻፈ ማስጠንቀቂያ የአገልግሎት ክፍያ ከፍሎ ከስራ አሰናብቶናል፡፡ አመልካች እኛን ካሰናበተ በኋላ ሌሎች ሠራተኞችን የቀጠረ መሆኑን አረጋግጠናል፡፡ አመልካች ያለበቂ ምክንያት ከህግ ውጪ ከስራ ያሰናበተን በመሆኑ ደመወዝ ከፍሎ ወደስራ እንዲመልሰን ካልሆነም የስንብት እና የካሳ ክፍያ በድምሩ ብር 330,288 እንዲከፈል ይወሰንልን በማለት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…….
879
Documents to download
-
228917 (.pdf, 841.72 KB) - 63 download(s)