አቶ ሆርዶፋ ዴቲ እና ወ/ሮ ፀሐይ ሽፈራው የሰ/መ/ቁ፡-201929
ጉዳዩ የፍርድ አፈፃፀም ክስ መነሻ ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው ኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁን 1ኛ ተጠሪ የአፈጻጸም ከሳሽ፤የአሁኑ አመልካች በአፈጻጸም ተከሳሽ፤የአሁኑ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ደግሞ ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል፡፡የክርክሩ አመጣጥ ባጭሩ ሲታይ አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ ጋብቻቸው በፍቺ እንዲፈርስ ከተወሰነ በኋላ 200 ሄክታር የቡና ልማት የኢንቨስትመንት ይዞታ የጋራ ንብረት ነዉ ተብሎ እኩል እንዲካፈሉ ተወስኖ የፌዴራል ፍ/ቤቶች የአፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ንብረቱ ያለበት የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በውክልና ውሳኔውን እንዲያስፈጽም ትዕዛዝ መስጠቱን ተከትሎ የአፈፃፀም መዝገብ ቁ/42899 ተከፍቶ በሂደት ላይ እያለ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በየበኩላቸዉ ባልና ሚስቱ ከባንኩ ተበድረዉ ያልከፈሉት እዳ መኖሩን በተለያየ መዝገብ ያሰጡትን ፍርድ በማቅረብ ንብረቱ በባልና ሚስት መካከል ክፍፍል ከመደረጉ በፊት እዳዉ እንዲከፈላቸዉ አቤቱታ በማቅረብ የክርክሩ ተካፋይ መሆናቸዉን መዝገቡ ያሣያል፡፡……………….
12565
Documents to download
-
201929(.pdf, 558.52 KB) - 912 download(s)