አቶ በፍቃዱ ጌታቸው እና እነ አቶ ዮናስ ጌታነህ የሰ/መ/ቁ196346
ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካች መስከረም 22 ቀን 2013 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 182644 ሰኔ 12 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ቅሬታውን በማቅረቡ ነው፡፡ ቅሬታውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካች የሚቃወምባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችሎት በኩል ሊታይልኝ ይገባል የሚለውን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ ያከራከረን ቤት በእናቴ ስም የተመዘገበ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ ጣልቃ ገብዎች ቤቶቹን ሰራን የሚሉት 1ኛ ጣ/ገብ አያቴ ሞግዚቴ ሆኖ ባለበት ጊዜ መሆኑ እየታወቀ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ያላደረኩትን እርቅ መሰረት አደርጎ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ የሚል ነው፡፡……..
15270
Documents to download
-
196346(.pdf, 1.04 MB) - 1258 download(s)