አቶ ታሪኩ ዮናስ እና ዳንጎቴ ኢትዮጵያ ሲምንቶ ፋብሪካ የሰበር መ/ቁ/200247
ጉዳዩ የአሰሪና ሠራተኛ የስራ ክርክር የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አደዓ በርጋ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን የተከራከሩበት ነዉ፡፡አመልካች 02/06/2012 ዓ.ም ባቀረበው ክስ ተጠሪ በሰው ኃይል አስተዳደር የሥራ ዘርፍ በደብዳቤ ቁጥር DI-HR-009-14 ሕዳር 24 ቀን 2007 ዓ.ም በወር ደመወዝ ብር 7,100 የቀጠረኝ ሲሆን የሥራ ብቃት ምዘናዬ ከፍተኛ ስለሆነ በተለያየ ጊዜ እድገት ሰጥቶኝ በመጨረሻ በወር ደመወዝ ብር 29,980.14 እየሰራዉ እያለ ታህሳስ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ያለአንዳች ጥፋት ከስራዬ ስላሰናበተኝ በአዋጅ ቁ/1156/2011 መሰረት ወደ ስራዬ እንዲመልሰኝ ወይም ካልመለሰኝ የተለያዩ ክፍያዎች በድምሩ ብር 435,711.34 እንዲከፍለኝ እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት የጠየቀ ሲሆን ተጠሪ በቀን 12/06/2012 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው መልስ አመልካች ከፍተኛ የኦፊሰር ስራ ዘርፍ እና የድርጅታችን የሰው ኃይል መመሪያ ኃላፊ በመሆን ሲሰራ ቆይቷል፣ሃላፊነቱ ሥራ አስኪያጅ የሆነ ሰው ደግሞ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 3(2ሐ) መሰረት በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መክሰስ ስለማይችል ክሱ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ እንዲሆን ጠይቋል፡፡……………..
13622
Documents to download
-
200247(.pdf, 744.02 KB) - 871 download(s)