አቶ ናሆም ተወልደ እና እነ ወ/ሮ ንግስቲ ገዛኽኝ የሰ/መ/ቁ 217149
መዝገቡ ዛሬ በችሎት የቀረበው 6ኛ ፣7ኛ 8ኛ ተጠሪዎች በግልና በጋራ ባቀረቡት የተሰጠ የዕግድ ይነሣልንና ወደ አከራካሪው ቤት እንድገባ ትዕዛዝ ይሰጥልኝ አቤቱታ የሚመለከታቸው አካላት ደርሷቸው አስተያየት እንዲያቀርቡ በዚህ ችሎት መታዘዙን ተከትሎ፤ 7ኛ እና 8ኛ ተጠሪዎች አመልካችን ማግኘት አለመቻላቸውን በመግለፅ ትአዛዙ ለአመልካች የሚደርስበት አማራጭ በመዘርዘር ባቀረቡት አቤቱታና 6ኛ ተጠሪ ባቀረቡት አቤቱታ ላይ አስተዳደሩ አስተያየት መስጠቱን ተከትሎ ትዕዛዝ እንዲሰጥበት በማስፈለጉ ነው፡፡በዚህ መሰረት ጉዳዩን መርምረን ተከታዩን ትዕዛዝ ሰጥተናል…………
13420