አቶ አበበ አድገህ እና እነ ወ/ሮ ዘሪቱ ደርሰህ የሰ/መ/ቁ፡- 199400
ጉዳዩ የቤት ሽያጭ ዉል መኖሩ በተካደ ጊዜ በማስረጃነት ሊቀርብ የሚገባዉን ዉል አይነት የሚመለከት ነዉ፡፡አመልካች በምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች ላይ በመሰረቱት ክስ ከ1ኛ ተጠሪ እና ከተራ ቁጥር 2-5 ድረስ የተጠቀሱ ተጠሪዎች አባት ከሟች አቶ ተገኘ ፀሐይ ጋር በቀን 13/10/1987 ዓ/ም በተጻፈ የቤት ሽያጭ በደንበጫ ከተማ ዉስጥ አዋሳኙ በክሱ የተጠቀሰዉን ስፋቱ 5 ሜትር በ10 ሜትር ወይም 50 ካሬ ሜትር ላይ የተሰራ በሟች አቶ ተገኘ ፀሐይ ስም ተመዝግቦ የሚገኘዉን 32 ዚንጎ የቆርቆሮ ቤት በብር 10,000.00 ሽጠዉልኛል፡፡ገንዘቡን በእለቱ ተረክበዉ የሽያጭ ዉሉን በደንበጫ ከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት አስገብተነዉ በፋይሉ ዉስጥ ይገኛል፡፡ቤቱን በግዥ ያገኘሁ ስለመሆኑ በተለያዩ ጊዜ የታመነ እና የተረጋገጠ ቢሆንም አሁን ላይ በቤቱ ለመጠቀም ስፈልግ የተለያዩ ተግባራትን እንዳላከናዉንና የቤቱ ስመ ሀብት በስሜ ዞሮ እንዳይመዘገብ ተጠሪዎች ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡ስለሆነም ተጠሪዎች በሚመለከተዉ አካል ፊት ቀርበዉ የቤቱን ስመ ሀብት በስሜ እንዲያዛዉሩልኝ እንዲወሰንልኝ፡፡ዉሉ የሚፈርስበት ምክንያት አለ ከተባለም ቤቱ በአሁኑ ጊዜ የሚያወጣዉን የዕለት ዋጋ ብር 200,000.00 እንዲከፍሉኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡.........................
13334
Documents to download
-
199400(.pdf, 745.84 KB) - 1317 download(s)