አቶ ወርቁ ኃይለመስቀል እና አቶ ከበደ ደስታየሰ/መ/ቁ፡-198805
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሠበር ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር ተከሳሽ ሲሆኑ ተጠሪ ከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ከሟች አባታቸው አቶ ደስታ አድማሱ በውርስ የሚተላለፍ የሚንቀሳቀስ እና በዚህ ችሎት ደረጃ አከራከሪ ሆነ የቀረበውን የገጠር እርሻ መሬት አመልካች ለቀው እንዲያስረክቧቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ አመልካች ስለመሬቱ ያቀረቡት መልስ ይዞታው የሟች ደስታ አድማሱና የባለቤቱና የአመልካች አያት የሆኑት የወ/ሮ እህተጊዮርጊስ ኃይለጊዮርጊስ ሲሆን አያቴ ወራሽ ስለሆን የሟች ደስታ አድማሱን ድርሻ በኑዛዜና በሥጦታ አስተላፈውልኛል፡፡ በድጋሜ ከልጆቹ ጋር መሬቱን አውርሰውኛል፡፡ የሟች ደስታ ድርሻ ሊተላፍልህ አይችልም ቢባል እንኳን የአያቴ የቤተሰብ አባል ስለሆንኩ ግማሽ ድርሻውን ተጠሪ ሊጠይቁኝ አይገባም ብለዋል፡፡ ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የወረዳ ፍርድ ቤት ጉዳዩን መርምሮ…………….
13564
Documents to download
-
198805(.pdf, 727.78 KB) - 907 download(s)