አቶ ጌታቸው ሀይሉ እና የኢትዮጵያ የባህር ትራንፖርትና ሎጅስትክስ አገልግሎት ድርጅት የሰ/መ/ቁ፤-206283
ጉዳዩ የዲስፕሊን ዉሳኔ በመቃወም የቀረበ ክስ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ ተጠሪ ላይ ባቀረበው ክስ ነዉ፡፡የክሱ ይዘት ባጭሩ በተጠሪ ድርጅት ውስጥ ከታህሳስ 26 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ በከባድ መኪና ሹፌር የስራ መደብ ተቀጥሬ በማገልገል ላይ ሳለሁ ነሐሴ 6 ቀን 2010 ዓ.ም ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ እያሽከረከርኩ እያለ በጅቡቲ ውስጥ አርታ(ዊያ) በተባለ ቦታ የመልከዓ ምድሩ አቀማመጥ አስቸጋሪ ቁልቁለትና መታጠፊያ በሆነበት ቦታ ሌላ መኪና ደርቦ የእኔን መስመር ይዞ በመምጣቱ አደጋውን ለመከላከል በድንገት ፍሬን ሲያዝ አደጋ ያጋጠመ ሲሆን አደጋው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት የደረሰ ስለመሆኑ ከጅቡቲ ሪፐብሊክ የመንገድ ደህንነት የሰጠው የምርመራ ሪፖርት የሚያረጋግጥ ቢሆንም የተጠሪ ድርጅት የዲስፕሊን ኮሚቴ ከባለሙያ ሪፖርት ውጭ እና አመልካች ሃሳብ ባልሰጠሁበት ሁኔታ በንብረት ላይ የደረሰው አደጋ ግምት ዋጋ ብር 2,820,778.92 መሆኑን የዚህን ግምት ዋጋ 3% ሂሳብ ከአመልካች ደመወዙ በየወሩ 1/3ኛ እየተቀነሰ እንዲከፍል ውሳኔ አስተላልፎ ከሀምሌ ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ እየተቆረጠ ይገኛል፣ በመሆኑም በተጠሪ ንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት በመድን ፖሊሲው ሽፋን መሰረት ንብረቱ ተጠግኖ እያለ ያለአግባብ የአደጋ ተጠያቂና ጥፋተኛ በማድረግ የተወሰነብኝ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እንዲነሳልኝ እና የአደጋው ግምት 3% እንዲከፍል የተወሰነብኝ ከህግ ውጭ ነው ተብሎ የተቆረጠውም እንዲመለስልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቆ ተጠሪ በበኩሉ የፖሊስ ማስረጃ አመልካች አደጋውን ማስቀረት ወይም መቀነስ በሚችልበት ሁኔታ አደጋው የተከሰተ በመሆኑ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ነዉ በማለት ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት እንደሌለዉ፣አመልካች ለዲስፕሊን ክስ የጽሁፍ መልስ፣ ከፖሊስ ሪፖርት ጋር እንዲሁም ከህብረት ስምምነት ድንጋጌ ጋር በማጣራት የፈፀመው ጥፋት ከስራ የሚያሰናብተው ቢሆንም ያለፈ መልካም አገልግሎት ግምት ውስጥ በማስገባት አመልካች ላይ የተወሰደው አስተዳደራዊ የቅጣት እርምጃ ተገቢ እና ህጋዊ በመሆኑ ሊነሳ አይገባም በማለት ተከራክረዋል፡፡…………
8633
Documents to download
-
206283(.pdf, 1.09 MB) - 760 download(s)