አቶ ግደይ ገ-ጻድቃን ገ-ማርያም እና ወ-ሮ ክንድሀፍቲ ኢታይ የሰ-መ-ቁ 179589
የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 24172 በቀን 08/04/2011 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ እና የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 226191 በቀን 19/07/2011 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው፡፡ ክርክሩ የዕግድ ትዕዛዝ እንዲነሳ በአመልካች የቀረበን አቤቱታ የሚመለከት ነው፡፡በፌዴራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በከሳሽ ወ/ሮ ክንድሀፍቲ ኢታይ (የአሁን ተጠሪ) እና በተከሳሽ አቶ ፀጉ ብርሃነ መካከል በነበረው የባልና ሚስት የንብረት ክርክር ጉዳይ የአሁን ተጠሪ ንብረት እየሸሸ በመሆኑ ይታገድልኝ በማለት በፀጉ ብርሃነ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሚታወቁ መኪኖች ላይ የእርድ ትዕዛዝ አሰጥተዋል፡፡በፀጉ ብርሃነ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እግዱ እንዲነሳ ጠይቆም በቅድሚያ ዋስትና እንዲያስይዝ ተጨማሪ ትዕዛዝ ተሰጥቶበታል፡፡…..
13661