እማሆይ አዛል አይናለም እና አቶ ምህረት በላይ የሰ/መ/ቁ.200144
ጉዳዩ የስጦታ ውል እንዲፈርስ የቀረበ ክስ የሚመለከት ነዉ፡፡ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከሳሽ በመሆን የአሁኑ ተጠሪ 1ኛ ተከሳሽ እንዲሁም የቡሬ ወረዳ መሬት አጠቃቀም እና አስተዳደር ጽ/ቤት 2ኛ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡የአመልካች ክስ ይዘት ባጭሩ ለተጠሪ ያደረግሁለት የሥጦታ ውል በመንፈስ ልልነት እና በዕድሜ የገፋሁ አቅመ ደካማ በመሆኔ ምክንያት ከፈቃዴ ውጭ ህጉን ሳይከተል ያደረግሁት በመሆኑ እና በስር 2ኛ ተከሳሽ ከአሁኑ ተጠሪ ጋር በመመሳጠር የስጦታ ውሉን ያፀደቀ በመሆኑ የስጦታ ውሉ ይፍረስልኝ በማለት ዳኝነት የጠየቁ ሲሆን ተጠሪ ባቀረበዉ መልስ አመልካች በፈቃዷ ስጦታውን ያደረገችለት መሆኑን እና ክሱ የቀረበው የአመልካች ልጆች ከቅን ልቦና ውጭ በሆነ ሁኔታ መሬቱን ለመውሰድ በማሰብ ነዉ፤የስጦታ ውሉ የሚፈርስበት የህግ ምክንያት የለም በማለት ተከራክረዋል፡፡……………….
13326
Documents to download
-
200144(.pdf, 526.94 KB) - 1335 download(s)