እነ ሀድሌ ኢብራሂን እና እነ የጠይብ አብዲላሂ ሰ/መ/ቁ. 202114
ጉዳዩ እርሻ መሬትን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የጀመረውም በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋፈን ዞን ጅግጅጋ ወረዳ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በስር ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር አመልካቾች ከሳሽ፣ ተጠሪዎች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ አመልካቾች በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡተ ክስ በሰሀሊቲ ቀበሌ ኮጃርታ ሼህ ጣሂር ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ በሰሜን ሀጂ መሀመድ እና የጎሳ ቦታ፣ በምዕራብ ሙሳ አውሌ፣ በደቡብ ተጠሪዎች፣ በምስራቅ የአመልካቾች መሬት የሚያዋስኑትን ስፋቱ 4 ጋሻ፣ ርዝመቱ ደግሞ 7.5 ጋሻ ጠቅላላ መጠኑ 30 ጋሻ የሆነ የእርሻ መሬት ያለአግባብ ይዘውብናል፤ እንዲለቁልን ብንጠይቃቸው ፍቃደኛ ስላልሆኑ ለቀው እንዲያስረክቡን ይወሰንልን በማለት ዳኝነት ጠይቀው ተከራክረዋል፡፡…………
7625
Documents to download
-
202114(.pdf, 817.73 KB) - 798 download(s)