Login
Federal Supreme Court of Ethiopia
Search
  • Home
  • About Us
    • President Message
    • President
      • Current President
      • Former President
    • Vice President
      • Current Vice President
      • Former Vice Presidents
    • History and Traditions
    • Judges
      • Former Judges
    • Vision Mission and Mandate
    • Judicial Administration Council
  • Court Services
    • Registry Services
      • Court Forms and Fees
    • Daily Court Trial Schedule
    • Case Tracker
    • Requesting Court Documents
      • Disposed Cases
    • Court Annexed Mediation
    • Interpretation Services
    • Legal Support
      • Child Justice Project Office
      • Public Defenders Office
  • Going to Court
    • Visiting the Court
      • What Can I see and Do?
    • Courtroom Etiquette
      • Courtroom Rules
    • Criminal: Information for the Accused Person
    • Civil Disputes: Information for Parties
    • Representing Yourself
    • Information for Witness
    • Information for Lawyers
    • FAQ
  • Digital Law Library
    • Annual Reports
    • State of the Judiciary
    • Monthly Judges Seminar
    • Federal Laws
    • Archives
    • Publications
      • Journal
      • Federal Cassation Decision Series
      • Newsletter
    • Judgments
      • Cassation Decisions
      • Supreme Court Decisions
  • News Media
    • Announcements
    • Interactives
      • Photos
      • Video
    • Services for Media
      • Press Releases
      • Press Conference
      • Media Advisories
      • Speeches
    • NEWS
  • Contacts
    • Federal Supreme Court
    • Federal High Court
    • Federal First Instance Court
    • Contact and Feedback
  • Tender
  • Judgement Execution Directorate
    • About Judgement Execution Directorate
    • Auction
  • Vacancy
  • Child Justice Project
Wednesday, February 3, 2021
/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

እነ አቶ አየናዉ አላምረዉ ወ-ሮ መሰረት ሉሉ የሰ-መ-ቁ 183394

ይህ የወጪና ኪሳራ፣ የተቋረጠ ገቢን የሚመለከት ክርክር የተጀመረዉ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን፣ የአሁን አመልካች የሥር ተከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ የሥር 1ኛ ከሳሽ፣ በዚህ ችሎት የክርክሩ ተካፋይ ያልሆነዉ መርጌታ ታዬ ሉሉ ሌሎች የሥር 2ኛ ተከሳሽ ሆኖ ሲከራከሩ ነበር። ጉዳዩ ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለዉ የአሁን አመልካች የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ.300510 በ02/11/2011 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዲታረምልኝ በማለት በማመልከታቸዉ ነዉ።

የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ በሥር ከሳሾች እና በሥር ተከሳሽ መካከል የነበረዉን የወጪና ኪሳራ እንዲሁም ከቤት ጋር በተያያዘ የተቋረጠ ገቢን የሚመለከት ክርክር የሥር የከፍተኛ ፍ/ቤት ግራ ቀኙን አከራክሮ ዉሳኔ ከሰጠ በኋላ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.208 መሰረት የቀረበዉን አቤቱታ ተከትሎ ጉዳዩን ድጋሚ በማየት በመ.ቁ.61826 በ16/9/2010 ዓ.ም በሰጠዉ ዉሳኔ የሥር ተከሳሽ በክርክሩ ምክንያት በሥር ከሳሻ ላይ ለደረሰዉ ወጪና ኪሳራ ብር 210.00 [ሁለቶ አስር] እንዲከፍላት፤ የታጠዉን የቤት ኪራይ ገቢን በተመለከተ የተጠየቀዉ ዳኝነት የክስ ምክንያት ስለሌለዉ ዉድቅ ነዉ በማለት ወስኗል። የሥር 1ኛ ከሳሽ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረበች ቢሆንም ፍ/ቤቱ ይግባኙን በትዕዛዝ ዉድቅ በማድረግ የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። የሥር ከሳሽ አሁንም በዚህ ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታ ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረበች ሲሆን ችሎቱም ግራ ቀኙን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ የሥር የከፍተኛዉ ፍ/ቤት የሥር ተከሳሽ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.208 መሰረት ያቀረበዉን አቤቱታ ተቀብሎ የቀደመዉን ዉሳኔ በመሻር የሰጠዉ ዉሳኔ የሕግ ድጋፍ የለዉም በማለት በመሻር ወስኗል። የአሁን ሰበር አቤቱታ የቀረበዉ በዚህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ለማስለወጥ ነዉ። የአሁን አመልካች ባቀረበዉ የሰበር አቤቱታ፡ ግራ ቀኙ አንድ ክልል ነዋሪዎች በመሆናችን የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ይህን ጉዳይ ለማየት ስልጣን እንደሌለዉ የአሁን አመልካች ለክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ባቀረበዉ መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አንሶቶ ነበር። የሥር የክልሉ ከፍተኛ ፍ/ቤትም ሆነ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ጉዳይ ያዩት በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 80 [2፣ 4] መሰረት በተሰጠዉ የዉክልና ስልጣን በሆኑ፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በሰጠዉ ዉሳኔ ቅሬታ መቅረብ ያለበት በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 [1] መሰረት ለፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት ሆኖ ሳለ የሥር የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ይህን መቃወሚያ በዝምታ በማለፍ የሰጠዉ ዉሳኔ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.244 [1] እና በዚህ ችሎት ከተሰጠዉ አስገዳጅ የህግ ትርጉም የሚቃረን ነዉ። ስለሆነም የሥር የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ይህን ጉዳይ በሰበር አይቶ ለመወሰን ስልጣን ሳይኖረዉ የሰጠዉ ዉሳኔ ሕጋዊ መሰረት የሌለዉ ስለሆነ እንዲሻርልኝ በማለት በዝርዝር አመልክቷል።............

Previous Article እነ አቶ ሳሙኤል ገዛኸኝ፣ አቶ መኩሪያ ታረቀኝ እና አቶ ፍሰሃ እርቅይሁን የሰ-መ-ቁ-191141
Next Article እነ አቶ ሳሙኤል ገዛኸኝ፣ አቶ መኩሪያ ታረቀኝ እና አቶ ፍሰሃ እርቅይሁን የሰ-መ-ቁ-191141
Print
18078

Documents to download

  • እነ አቶ አየናዉ አላምረዉ ወ-ሮ መሰረት ሉሉ የሰ-መ-ቁ 183394(.pdf, 510.2 KB) - 1223 download(s)

Categories

  • 2011 Expand/Collapse
  • 2012 Expand/Collapse
  • 2013 Expand/Collapse
    Contacts
  • TEL : +251-11-1-55-34-00 /
  •          +251-11-1-11-04-32
  • Fax : +251 111-550278 /
  •          +251 111-565583
  • Email : fscpublicrelation@gmail.com
  • Address: 6 Killo , Addis Ababa, Ethiopia
Quick Links
  • About Us
  • E-Filing 
  • Calendar
  • Press Release
  • Case Tracker
  • FAQ
    Connect With Us
  • Privacy Policy
  • |
  • Site Map
Copyright © The Federal Supreme Court of Ethiopia- All rights reserved
Powered By Bsquare IT Solutions