እነ አቶ ካሳሁን ዘላለም እና የሰሜን ሸዋ ዞን የገቢዎች ዓቃቤ ሕግ የሰ.መ.ቁ 208826
ጉዳዩ ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው፡፡ የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካቾች ላይ በስር ፍርድ ቤት ያቀረባቸው ክሶች ሶስት ሲሆኑ ይዘታቸውም፡-
1ኛ ክስ፡- 1ኛ አመልካች የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 120/1 ድንጋጌን በመተላለፍ በደብረብርሃን ከተማ ቀበሌ 06 ገቢዎች ጽ/ቤት በተጨማሪ እሴት ታክስ ግብር ከፋይነት ተመዝግቦ በሬስቶራንት ንግድ ዘርፍ ተሰማርቶ በመስራት ላይ እንዳለ ሕዳር 08 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 7፡15 ሠዓት ሲሆን በሬስቶራንቱ ውስጥ የምግብ እና የመጠጥ አገልግሎት ለመጠቀም የገቡት አቶ ተክልዬ አስራት እና አቶ ብርቅነርህ ደሳለኝ የተባሉት ግለሰቦች ሁለት ጥብስ፤ ሁለት ቢራ እና ሁለት ድራፍት ከተጠቀሙ በኋላ ለጥብሱ ብር 180፤ ለቢራው ብር 50፤ ለድራፍቱ ብር 24፤ በጠቅላላው ብር 254 / ሁለት መቶ ሀምሳ አራት / ከፍለው ሲወጡ ከሽያጭ መመዝገቢያው መሳሪያ የሚወጣውን ደረሰኝ ቆርጦ መስጠት ሲገባው ደረሰኙን ሳይሰጥ ግብይት የፈጸመ እና ወዲያውኑ እጅ ከፍንጅ የተያዘ በመሆኑ በፈጸመው ያለደረሰኝ ግብይት መፈጸም ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡…………
9200
Documents to download
-
208826(.pdf, 1.05 MB) - 1689 download(s)