እነ አቶ ዮሴፍ ኃይሌ እና ፎራንክ ቢዝነስ ግሩፕ አክሲዮን ማህበር የሰ/መ/ቁ. 209266
ጉዳዩ የስራ ስንብትን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በተጀመረበት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካቾች ከሳሽ፣ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ አመልካቾች በተጠሪ ላይ በቀን 22/10/2012 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ በተጠሪ ድርጅት ውስጥ በተለያየ የቅጥር ዘመን በሽያጭ ባለሞያ የስራ መደብ ላይ ተቀጥረን ስንሰራ ብንቆይም ተጠሪ ከህግ ውጪ ከቀን 26/08/2012 ዓ.ም ጀምሮ አሰናብቶናል፡፡ ስለሆነም ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው ተብሎ ተጠሪው ካሳ፣ የአገልግሎት፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ ቅጣት፣ ከግንቦት ወር ጀምሮ የኮሮና ወረርሺኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እስከሚበቃበት ጊዜ ድረስ ያለው የወር ደመወዛችን እና የዓመት እረፍት በገንዘብ ተቀይሮ እንዲከፈለን ይወሰንልን በማለት የጠየቁትን ዳኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ፡፡እንደሚከተልው ቀርቧል…………….
14090
Documents to download
-
209266(.pdf, 823.85 KB) - 1120 download(s)