እነ ወ/ሮ ከበቡሽ ቡሎየ እና አቶ መንግሥቱ ባለህ ሰ/መ/ቁ. 202681
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካቾች የስር ከሳሾች ሲሆኑ ተጠሪ ተከሳሽ ነበሩ፡፡ አመልካቾች ያቀረቡት ክስ በተጠሪ የንግድ ሥራ በልብስ ስፌት፣ በልብስ እጅ ሥራና ዝምዘማ የሥራ መደብ ተቀጥረን ስንሰራ ነሀሴ 28 ቀን 2011 ዓ/ም ከሕግ ውጭ በቃል ከሥራ አሰናብቶናል፡፡ የሥራ ስንብቱ ሕገ-ወጥ ስለሆነ የአገልግሎት ክፍያ፣ ካሣ፣ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ የዓመት ዕረፍት፣ ትርፍ ሰዓት የተሰራበት ክፍያ እንዲሁም ክፍያው ለዘገየበት ቅጣት እንዲከፈላቸው እና የሥራ ልምድ እንዲሰጣቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡………..
7187
Documents to download
-
202681(.pdf, 838.04 KB) - 663 download(s)