እነ ወ/ሮ የብርጓል በላይነህ እና እነ ወ/ሮ እቴነሽ መብራት የሰ/መ/ቁ፡-203809
ጉዳዩ የይግባኝ ማስፈቃጃ አቤቱታን የሚመለከት ነው፡፡ የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካቾች የአዊ ብሔረሰብ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 01-18421 ሕዳር 11 ቀን 2012 ዓ/ም በሠጠው ውሳኔ ይግባኙን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለማቅረብ የ60 ቀናት ጊዜው ያለፈባቸው በመሆኑ ጥር 20 ቀን 2013 ዓ/ም በተጻፈ ማመልከቻ የይግባኝ ማስፈቀጃ አቤቱታ በማቅረብ ጊዘው ያለፈው የኮሮና ወረሽኝ በሽታ በመኖሩ፣ በሚኖሩበት አካባቢ የጸጥታ ችግርና የትራንስፖርት ችግር ያጋጠማቸው መሆኑን በመጥቀስ ከአቅም በላይ የሆኑ ምክንያቶች መሆናቸውን በማንሳት ይግባኙን ማቅረብ እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል፡፡…………..
12477
Documents to download
-
203809(.pdf, 828.94 KB) - 1036 download(s)