እነ ወ-ሮ ጀማነሽ ቀነኒ፣አቶ አሰፋ ሸቡ እና ወ-ሮ ብርቱካን ሸቡ የሰ-መ-ቁጥር 177205
ለዚህ የሰበር መዝገብ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ የቀረበው አመልካች ግንቦት 12 ቀን 2011 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ የደቡብ ብ/ብ/ህ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 11920 የካቲት 12 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ እና የደቡብ ብ/ብ/ህ/መ. ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁጥር 12667 ግንቦት 5 ቀን 2011 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልን በማለት ቅሬታቸውን በማቅረባቸው ነው፡፡ ቅሬታቸውም አቤት የተባለበትን ውሣኔ፣ አመልካቾች የሚቃወሙባቸውን ምክንያቶች የሚዘረዝርና በሰበር ሰሚው ችሎት በኩል ሊታይልን ይገባል የሚሉትን ዳኝነት የሚጠይቅ ሲሆን፣ የስር ፍ/ቤት የከተማ ማዘጋጃ ቤቱ አጣርቶ ገልጾ እያለ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ከቀበሌ ጠይቆ በዚሁ ተመስርቶ የሰጠው ውሳኔ ተገቢ አይደለም፡፡ የውርስ አጣሪው ከሳሽ 12,000 ብር የተቀበለች መሆኑን ጭምር ከሪፖርቱ ጋር ሰነዱን አቅርቦ እያለ እና ድርሻዋን መውሰዷ ተረጋግጦ እያለ በድካሚ ትካፈል ተብሎ መወሰኑ ተገቢ ባለመሆኑና የተጠሪ ክስም በይርጋ ውድቅ መሆን ስገባ መታለፉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ይታረምልኝ የሚልነው፡፡...........
13481