Login
Federal Supreme Court of Ethiopia
Search
  • Home
  • About Us
    • President Message
    • President
      • Current President
      • Former President
    • Vice President
      • Current Vice President
      • Former Vice Presidents
    • History and Traditions
    • Judges
      • Former Judges
    • Vision Mission and Mandate
    • Judicial Administration Council
  • Court Services
    • Registry Services
      • Court Forms and Fees
    • Daily Court Trial Schedule
    • Case Tracker
    • Requesting Court Documents
      • Disposed Cases
    • Court Annexed Mediation
    • Interpretation Services
    • Legal Support
      • Child Justice Project Office
      • Public Defenders Office
  • Going to Court
    • Visiting the Court
      • What Can I see and Do?
    • Courtroom Etiquette
      • Courtroom Rules
    • Criminal: Information for the Accused Person
    • Civil Disputes: Information for Parties
    • Representing Yourself
    • Information for Witness
    • Information for Lawyers
    • FAQ
  • Digital Law Library
    • Annual Reports
    • State of the Judiciary
    • Monthly Judges Seminar
    • Federal Laws
    • Archives
    • Publications
      • Journal
      • Federal Cassation Decision Series
      • Newsletter
    • Judgments
      • Cassation Decisions
      • Supreme Court Decisions
  • News Media
    • Announcements
    • Interactives
      • Photos
      • Video
    • Services for Media
      • Press Releases
      • Press Conference
      • Media Advisories
      • Speeches
    • NEWS
  • Contacts
    • Federal Supreme Court
    • Federal High Court
    • Federal First Instance Court
    • Contact and Feedback
  • Tender
  • Judgement Execution Directorate
    • About Judgement Execution Directorate
    • Auction
  • Vacancy
  • Child Justice Project
Friday, December 4, 2020
/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

እነ ወ-ሮ ፈይዛ ከማል አወል፣አቶ አብዲ አህመድ መሀመድ እና አቶ ካህሳይ ተስፋዝጊ የሰ-መ-ቁ 184601

ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ ሊቀርብ የቻለው አመልካች የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ን/ስ/ላ/ምድብ በኮ.መ.ቁ 88409 በ16/2/11ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ እና የፌ/ከ/ፍ/ቤት በኮ.መ.ቁ 222352 በ19/11/11ዓ.ም በሰጠው ብይን/ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት በ11/2/12ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡የጉዳዩ አመጣጥ አመልካች በስር የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የን/ስ/ላ/ ምድብ 4ኛ ፍ/ብሄር ችሎት በ1ኛ ተጠሪ ላይ ጋብቻቸው በፍ/ቤት በ23/4/07ዓ.ም በተሰጠ ውሳኔ በፍቺ መፍረሱን ተከትሎ ባቀረቡት የጋራ ንብረት ክፍፍል ክስ አከራካሪውን የሰ.ቁ ኮድ A-13872 ያሪስ መኪና ዋጋው ብር 550‚000 የሚያወጣ እና ሌሎች ንብረቶችን የእቁብ ገንዘብን ጨምሮ በመዘርዘር ንብረቶቹ የጋራችን ስለሆኑ እኩል እንድንካፈል እንዲወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀው 1ኛ ተጠሪ ባቀረቡት መልስ በጋብቻ ውስጥ እያለን በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ቀበሌ 13 የቤት ቁጥር 069 በአቶ መሃመድ ይማም ዳኝነት በአቶ እንድሪስ አለሙ ጸሀፊነት በአቶ ወንድሜነህ አለሙ ይሰበሰብ የነበረው እቁብ በ29/4/04ዓ.ም ደርሶኝ ለትዳራችን ጥቅም ያዋልኩት ሲሆን፤ ይህን እቁብ መክፈል ባለመቻሌ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ፍ/ብሄር ችሎት በመ.ቁ 38976 ክስ ቀርቦብኝ ገንዘቡን እንድከፍል በ30/4/05ዓ.ም ተወስኖብኝ ከነወጪና ኪሳራ ብር 149‚365.95 እንድከፍል በመገደዴ አመልካች ያካፍለኝ በማለት ያቀረበችውን የሰ.ቁ ኮድ2- A13872 የሆነውን መኪና ሸጬ እዳውን ከከፈልኩኝ በኋላ ቀሪውን ገንዘብ ለትዳር ጥቅም ስለዋልኩት ጥያቄው አግባብ አይደለም በማለት ተከራክረው እንዲሁም በሌሎች ንብረቶችም ላይ መልስ የሰጡ ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራቀኙን በቃል ካከራከረ በኋላ ግራቀኙ በጋብቻ እያሉ የጋራቸው የሆነ እዳ ነበር ወይስ አልነበረም? አከራካሪውን የሰ.ቁ ኮድ2- A13872 የሆነውን መኪና ግራቀኙ በትዳር እያሉ ተሸጦ ለጋራ እዳ ክፍያ እና ለትዳር ጥቅም ውሏል ወይንስ አልዋለም? የሚለውን እና ሌሎች ንብረቶችን በተመለከተ የተለያዩ ጭብጦችን በመያዝ፤ አከራካሪውን መኪና በተመለከተ ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል ትእዛዝ በመስጠት ምላሽ ከቀረበለት በኋላ ጉዳዩን መርምሮ የጋራ እዳን በተመለከተ 1ኛ ተጠሪ ከአመልካች ጋር በጋብቻ እያለን ለደረሰብኝ እዳ መክፈል ባለመቻሌ በፌ/መ/ደ/ፍቤት አራዳ ምድብ ችሎት በመ.ቁ 38976 በ30/4/05ዓ.ም ከወጪና ኪሳራ ጭምር ብር 149‚365.95 እንድከፍል ተወስኗል ያሉትን በተመለከተ እዳው የመጣው ባልና ሚስት በጋብቻ አብሮ እያሉ ስለመሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ እዳው የጋራቸው ነው በማለት ከወሰነ በኋላ ከላይ የተገለጸውን ገንዘብ እንዲከፈል የተወሰነው በ30/4/05ዓ.ም በመሆኑ ለዚህ እዳ መኪና ተሸጠ የተባለው በ2007ዓ.ም ነው፤ 1ኛ ተጠሪ መኪናው በእዳ ተይዞ ተገዶ ለመሸጡ ሆነ ገንዘቡ ከመኪና ሽያጭ ለመከፈሉ ምንም ማስረጃ አላቀረበም፤ እዳው ከተከፈለም እዳው የመጣው በጋብቻ እያሉ በመሆኑ በጋብቻ አብረው እያሉ እንደተከፈለ የሚቆጠር በመሆኑ መኪና ተሸጦ ተከፈለ በማለት 1ኛ ተጠሪ ያቀረቡትን ክርክር ባለመቀበል፤ የሰ.ቁ ኮድ2- A13872 የሆነውን ያሪስ የቤት መኪና አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ በጋብቻ እያሉ ያልተሸጠ እና ለጋራ እዳም ሆነ ለትዳር ጥቅም ያለመዋሉ ከመረጋገጡም በላይ 1ኛ ተጠሪ ተሸጧል ሲል ቢከራከርም መኪናው ከመሸጡ በፊት በፍ/ቤት በ13/2/07ዓ.ም የታገደ መሆኑን 1ኛ ተጠሪም የሚያውቀው በመሆኑ፤ ለመሸጡ የንፋስ ስልክ ላፍቶ የመንገድና ትራንስፖርት የሰጠው መረጃ ታማኝነት የሌለው እና ውድቅ የተደረገ በመሆኑ ቢሸጥ እንኳን አስቀድሞ በፍ/ቤቱ የታገደ በመሆኑ ተገቢነት የለውም በማለት፤ በ1ኛ ተጠሪ እጅ የሚገኘው የሰ.ቁ ኮድ2- A13872 የሆነውን ያሪስ የቤት መኪና የአመልካች እና የ1ኛ ተጠሪ የጋራ ንብረታቸው ነው በማለት፤ ክፍፍሉን በተመለከተ ከተስማሙ አንዱ ለሌላው ግምቱን በመስጠት ያስቀረው፤ በዚህ ካልተስማሙ መኪናው በሀራጅ ተሸጦ ገንዘቡን እኩል እንዲካፈሉ በማለት በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 90 መሰረት ውሳኔ የሰጠ ሲሆን ሌሎች ንብረቶችን በተመለከተም ውሳኔ ሰጥቷል፡፡………….

Previous Article እነ ወ-ሮ ሐመልማል ታመነ ወ-ሮ የምስራች ተካ እና አቶ ክፍሌ ተካ የሰ-መ -ቁ 184335
Next Article ህፃን ሒዳያ አማን መሀመድ እና አመተበል መሃመድ የሰ-መ-ቁ 185175
Print
17166

Documents to download

  • እነ ወ-ሮ ፈይዛ ከማል አወል፣አቶ አብዲ አህመድ መሀመድ እና አቶ ካህሳይ ተስፋዝጊ የሰ-መ-ቁ 184601(.pdf, 522.12 KB) - 1358 download(s)

Categories

  • 2011 Expand/Collapse
  • 2012 Expand/Collapse
  • 2013 Expand/Collapse
    Contacts
  • TEL : +251-11-1-55-34-00 /
  •          +251-11-1-11-04-32
  • Fax : +251 111-550278 /
  •          +251 111-565583
  • Email : fscpublicrelation@gmail.com
  • Address: 6 Killo , Addis Ababa, Ethiopia
Quick Links
  • About Us
  • E-Filing 
  • Calendar
  • Press Release
  • Case Tracker
  • FAQ
    Connect With Us
  • Privacy Policy
  • |
  • Site Map
Copyright © The Federal Supreme Court of Ethiopia- All rights reserved
Powered By Bsquare IT Solutions