ኦዲት ሰርቪስ ኮርፖሬሽን እና ፀጋ ረታ አስመጪ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር የሰ/መ/ቁ፡-197008
ክርክሩ የሽያጭ ውልን መነሻ ያደረገ ሲሆን ጉዳዩ በተጀመረበት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ አመልካች የካቲት 4 ቀን 2011 ዓ.ም ባቀረበው ክስ አመልካች የኮምፒዩተር እቃዎችን ለመግዛት ባወጣው ጨረታ ተጠሪ አሸንፎ እቃዎቹን አቅርቦ ክፍያ የተቀበለ ቢሆንም እቃዎቹን ከሰርቨሩ ጋር የሚያገናኙ ኬብሎችን ባለማቅረቡ ምክንያት እቃዎቹ የተፈለገውን አገልግሎት መስጠት አልቻሉም፡፡በመሆኑም ኬብሎቹን እንዲያቀርብ ወይም በወቅቱ የገበያ ዋጋ የእቃዎቹን ግምት ብር 182,900 ወጪና ኪሳራን ጨምሮ እንዲከፍል ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡ተጠሪ የካቲት 29 ቀን 2011 ዓ.ም በተፃፈ መልስ አመልካች እቃዎቹ ጉድለት ያለባቸው መሆኑን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በ1 አመት ውስጥ ክስ ስላላቀረበ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል የሚል የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርቧል እንደሚከተለው ቀርቧል…………
2036
Documents to download
-
197008(.pdf, 1007.51 KB) - 103 download(s)