ወ/ሮ ህብስት ምሕረቴ እና የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል ገቢዎች ቢሮ የሰ/መ/ቁ. 200178
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ሠራተኛ የነበሩ ሲሆን በወንጀል ተጠርጥረውና ተከሰው የነበረ ሲሆን በኋላም ከወንጀል ክሱ በፍርድ ቤት በነጻ በመሰናበታቸው ወደሥራ ለመመለስ አመልክተዋል፡፡ መሥሪያ ቤቱ በሰው ኃይል አስተዳደር ደንብ ቁጥር 79/2003 አንቀጽ 41 መሠረት በወንጀል ተጠርጥሮ ሥልጣን ባለው አካል በእስር ላይ የነበረና እስከ ሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ከወንጀል ነጻ መሆኑ ተረጋግጦ ወደሥራ ካልተመለሰ አገልግሎቱ ይቋረጣል በሚል በግልጽ የተቀመጠ በመሆኑና አመልካች በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ጥያቄውን ያላቀረቡ በመሆኑ ተቀብለን መድበን ለማሰራት አንችልም በማለት ጥያቄውን ውድቅ አድርጓል፡፡………….
13516
Documents to download
-
200178(.pdf, 744.45 KB) - 960 download(s)