ወ/ሮ መሰረት ተሻለ ገ/የስ እና ኮ/ል ኪዳነ ገ/ኪዳን ተወልደመድህን የሰ.መ.ቁ 227876
ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ የቀረበው አመልካች የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ 167024 በ8/2/14ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ እንዲሁም የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ 277884 በ30/6/14ዓ.ም በሰጠው ብይን ቅር በመሰኘት በ24/9/14ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው፡፡
የጉዳዩ አመጣጥ አመልካች ከተጠሪ ጋር የነበራቸው ጋብቻ በፍቺ ውሳኔ መፍረሱን ተከትሎ በስር የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በተጠሪ ላይ ባቀረቡት የክስ አቤቱታ በጋብቻ ወቅት በጋራ የተፈሩ ናቸው በማለት በመከላከያ ፋውንዴሽን ለመኮንኖች በጋራ ያስገነባው ባለ 3 መኝታ ቤት ከጋራ ገቢ ብር 128,000.00 ተቆጥቦ ቤቱ ተሰርቶ ያለቀና በቅርብ ርክክብ የሚደረግበት ቤት ያለ በመሆኑ አመልካች ሁለት የጋራ ልጆቻችንን ይዤ ያለሁ ስለሆነ የዚህን ቤት የዋጋውን ግማሽ ለተጠሪ ከፍዬ ቤቱ እንዲሰጠኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ ሌሎች ንብረቶችን ገንዘብን ጨምሮ በመዘርዘር ከተጠሪ ጋር እኩል እንዲካፈሉ እንዲወሰንላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ የጋራ እዳ ናቸው ያሉትን ገንዘብ በመግለጽ ተጠሪ ግማሹን እንዲከፍሏቸው እንዲሁም ለተጠሪ ልኬያለሁ ያሉትም ገንዘብ እንዲመለስላቸው እንዲወሰንላቸው ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡ የልጅ ቀለብንም በተመለከተ ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡መልካም ንባብ…….
924
Documents to download
-
224876(.pdf, 1.02 MB) - 92 download(s)