ወ/ሮ የማርውሃ ወርቅነህ እና እነ ወ/ሮ ዓለም ወርቅነህ የሰ.መ.ቁ 242314
የጉዳዩ አመጣጥ ባጭሩ ሲታይ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች ከሳሽ አመልካች ደግሞ ጣልቃ ገብ ሆነው ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪዎች በቀን 11/09/2013 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት አቤቱታ የእናታቸው ወ/ሮ ሸዋነሽ ስመኝ ድልነሳው የውርስሀብት ተጣርቶ እንዲቀርብ አመልክተው አመልካች ወደ ክርክሩ በውርስ ማጣራት ሂደት በጣልቃ ገብነት ገብተው የውርስ አጣሪ ሪፖርቱ ከቀረበ በኋላ ግራ ቀኙ አስተያየት እንዲሰጡበት ተደርጓል፡፡ 1ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች በሰጡት አስተያየት የሟች እናታችን ውርስ እንዲጣራ በዉርስ አጣሪ ባቀረብነው አቤቱታ ላይ ምስክሮች ቀርበው ይሰሙ በማለት አስተያየት ሰጥተዋል መልካም ንባብ…
4266