ወ/ሮ ያምሮት አያና እና አቶ አዲሱ አያና የሰ.መ.ቁ.227111
የጉዳዩ አመጣጥ ሲታይ ከሳሽ በሥር ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ተከሳሽ የሟች አባታችን አቶ አያና አስማረ ልጅና ወራሽ መሆኑን በማረጋገጥ የዉርስ ሀብት ድርሻ ይገባኛል በማለት ዳኝነት በመጠየቅ የተወሰነለት ቢሆንም ተከሳሽ ተወለድኩኝ በሚልበት ጊዜ አባታችን በጸና ታሞ ያለና ከሌላ ግለሰብ ጋር ግንኙነት አድረጎ የማያውቅ በመሆኑ የሟች ልጅ ስላልሆነ ተከሳሽ የወሰደዉ የወራሽነት ማስረጃ እንዲሰረዝልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቋል፡፡
ተከሳሽ ባቀረበዉ ክርክር ከሳሽ ከዚህ በፊት ተከሳሽ የሟች ልጅ አይደለም በማለት የወራሽነት ማስረጃ እንዲሰረዝብኝ ዳኝነት ጠይቀዉ ልጅነቴ የጸና በመሆኑ እና በዉርስ ሀብት ክፍፍል ክርክር ላይም ተመሳሳይ ክርክር ቢያነሱም ዉድቅ ተደርጎ ወራሽነቴ የተረጋገጠ በመሆኑ ድጋሚ የቀረበ ክስ ነዉ ፤ከሳሽ የተከሳሽ ካሳሽነት ክስ ሳያቀርቡና ከረጅም ጊዜ ክርክር በኋላ ይህንን ክስ ማቅረባቸዉ አግባብ አይደለም በማለት አቤቱታቸው ውድቅ እንዲደረግልኝ በማለት ተከራክሯል፡፡ ከሳሽ በበኩላቸዉ ባቀረቡት ክርክር ተከሳሽ ያቀረቡት መከራከሪያ ዉድቅ እንዲደረግልኝ በማለት ተከራክሯል፡፡መልካም ንባብ…….
819
Documents to download
-
227111(.pdf, 837.16 KB) - 43 download(s)