የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል ገቢዎች ቢሮ እና አቶ አዕምሮ ዘሪሁን የሰ/መ/ቁ.210727
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው ተጠሪ በባሕር ዳር ከተማ ገቢዎች መምሪያ የታክስ ኦዲትና የሕግ ማስከበር የሥራ ሂደት አስተባባሪነት ከነበሩበት ኃላፊነት ተነስተው ከደረጃ 9 ወደ ደረጀ 8 ዝቅ ብለው በሽያጭ መመዝገቢያ ኤክስፐርት ሆነው እንዲሰሩ በመመደባቸው ቅሬታ አቅርበው ተቀባይት በማጣቱ ለአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የአስተዳደር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ይግባኝ ጥፋት ሳይኖረብኝና የዲሲፕሊን ክስ ሳይቀርበብኝ ከሥራ መደቡ መነሳቴ ሆነ ከደረጃና ደመወዝ ዝቅ መደረጌ አግባብ አይደለም የሚል ሲሆን አመልካች ባቀረበው መልስ በደንብ ቁጥር 79/2003 አንቀጽ 9(4) መሠረት ማንኛውም የሥራ ሂደት አስተባባሪ በአሳማኝ ምክንያት ከኃላፊነት ሲነሳ ከያዘው መደብ ዝቅ ብሎ እንደሚመደብ ስለሚገልጽ በዚህ አግባብ የተከናወነ ነው ብሏል፡፡…………
16329
Documents to download
-
210727(.pdf, 831.51 KB) - 1339 download(s)