የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ-ክርስቲያን ኮሚሽን እና አቶ መስፍን አዱኛ የሰ/መ/ቁ. 211260
ጉዳዩ የግል የስራ ቅጥር ዉልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በጀመረበት በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ በቀን 30/06/2013 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው ክስ በአመልካች ድርጅት ውስጥ ከጥር 23 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ በፕሮጀክት ኦፊሰርነት በወር ብር 10,095.00 እየተከፈለኝ ሳገለግል የቆየሁ ቢሆንም አመልካች ምንም አይነት ማስጠንቀቂያ ሳይሰጠኝ፣ በማላውቀው እና በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅምት 20 ቀን 2013 ዓ.ም የስራ ውሌን ያቋረጠው በመሆኑ ስንብቱ ህገ-ወጥ ነው ተብሎ ወደ ስራዬ እንድመለስ፤ ወደ ስራ የማልመለስ ከሆነ ደግሞ ያልተጠቀምኩበት የ58 ቀን የዓመት እረፍት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ፣ ካሳ፣ የሶስት ወር የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ ክፍያ ለዘገየበት የሶስት ወር ደመወዝ ቅጣት እንዲከፍል እና የስራ ልምድ እንዲሰጠኝ ይወሰንልኝ በማለት የጠየቀዉን ዳኝነት መነሻ ያደረገ ነዉ እንደሚከተለው ቀርቧል…………
13480
Documents to download
-
211260(.pdf, 825.29 KB) - 1049 download(s)