የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እና አበባየሁ ተዘራ የሰ.መ.ቁ 198703
ጉዳዩ የወንጀል ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው፡፡ አመልካች በተጠሪ ላይ በሥር ፍ/ቤት አቅርቦአቸው የነበሩት ክሶች ሁለት ሲሆኑ ይዘታቸውም፡-
1ኛ ክስ፡- ተጠሪ የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 543(3) እና ደንብ ቁጥር 208/2003 አንቀጽ 26 ድንጋጌዎች በመተላለፍ የሌላውን ሰው ሕይወት፣ ጤንነት እና ደሕንነት የመጠበቅ የሙያ ግዴታ እያለባት ባለመወጣት በቀን 23/07/2010 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 1፡30 ሠዓት ሲሆን የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 2-57534 አ.አ የሆነ ተሸከርካሪ እያሽከረከረች ከስድስት ኪሎ ወደ መገናኛ አቅጣጫ ስትጓዝ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ልዩ ቦታው ኮከበ ፅባሕ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ስትደርስ ለእግረኛ ቅድሚያ በመከልከል በእግረኛ ማቋረጫ መንገድ ላይ ስታቋጥ የነበረችውን ሟች አስምረት ንጉሴን በመኪናው የፊት ለፊት አካል ገጭታ በጭንቅላቷ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ራሷን ስታ ወድያውኑ ሕይወቷ እንዲያልፍ በማድረግ በፈጸመችው በቸልተኝነት ሰውን መግደል ወንጀል ተከሳለች የሚል ነው፡፡……….
7599
Documents to download
-
198703(.pdf, 830.74 KB) - 827 download(s)