ግርማ ለገሠ ተምትሜ እና የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የሰበር መ/ቁ/202092
ጉዳዩ የአሰሪና ሠራተኛ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች ከሳሽ ፤የአሁኑ ተጠሪ (ተከሳሽ) በመሆን ተከራክረዋል፡፡አመልካች በተጠሪ ድርጅት ውስጥ ከጥር 13 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ በሾፈር ስራ መደብ ላይ እየሰራሁ እያለሁ ተጠሪ ድርጅት የጡረታ መውጫ ጊዜህ ከሐምሌ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑን በቁጥር ፐ/ሰ/ድ/386/2011 በቀን 18/11/2011 ዓ.ም ስራዬን እንዳቆም በደብዳቤ በገለጸልኝ መሰረት አስፈላጊውን ፎርማሊቲ አሟልቼ ስራዬን ከለቀቅኩኝ በኋላ ጡረታ ሚኒስቴር በመመላለስ የጡረታ አበል ለመቀበል እንዲችል በምጠይቅበት ጊዜ የጡረታ መውጫ ጊዜዬ ሐምሌ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ሳይሆን ከሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑን ገልጸውልኝ ወደ ስራዬ እንዲመለስ ጡረታ ሚኒስቴር ለተጠሪ ሲጽፍ ተጠሪ ድርጅት ወደ ስራ እንዲመለስ እና ደመወዝ እንዲከፈለኝ ሲጠይቅ ፍቃደኛ ባለመሆኑ የጡረታ መውጫ ጊዜዬ እስኪደርስ ወደ መደበኛ ስራዬ እንዲመልሰኝ እና የተቋረጠብኝ ደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅም እንዲከፈለኝ እንዲወሰንልኝ የሚል ዳኝነት ያቀረበ ሲሆን ተጠሪ በበኩሉ የሰጠው መልስ የአመልካች ሥራ የተቋረጠው በተጠሪ ጥፋት ሳይሆን አመልካች ሲቀጠር የሕይወት ታርክ ቅጽ ሲሞላ የተወለደበት ቀን ራሱ የሞላው መሰረት ተድረጎ ስህተት የተፈጠረው አመልካች በሌላ ድርጅት ሲቀጠር የሞላው የትውልድ ዘመን እና በተጠሪ ድርጅት ሲቀጠር የሞላው የትውልድ ዘመን ሲጣራ የጡረታ እድሜ ያልደረሰ መሆኑን የጡረታ ሚኒስቴር ያረጋገጠ ሲሆን ተጠሪ ድርጅትም ከመስከረም 27 ቀን 2012 ዓ.ም ስራ እንዲጀምር ቢጠየቁም ውዝፍ ደመወዝ ካልተከፈለኝ በማለት ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡………..
7521
Documents to download
-
202092(.pdf, 834.9 KB) - 641 download(s)