ፌደራል ስነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን እና ወ/ሮ ፍሬህይወት ተረፈ የሰ/መ/ቁ፡- 209987
ጉዳዩ ተጠሪ በአመልካች ኮሚሽን አለአግባብ ከደረጃና ከደመወዝ ዝቅ ተደርጌያለሁ በማለት ለፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ አስተዳደር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ይግባኝ መነሻ የተሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ተብሎ የቀረበዉን የሰበር አቤቱታ የሚመለከት ነዉ፡፡ ተጠሪ በአመልካች ላይ በአስተዳደር ፍርድ ቤት ዘንድ ባቀረቡት ይግባኝ ከንብረት አወጋገድ፣ከሂሳብ አዘጋግ፣ በኦዲት ግኝት ለይ የተሰጠዉን ምክረ ሀሳብ ተግባራዊ ከማድረግ እና ሥራዎቼን በወቅቱ ከመፈጸም አንጻር የፈጸምኩት ጥፋት ሳይኖር አለአግባብ ከነበርኩበት ሥራ መደብ አንድ ደረጃ ዝቅ አድርጎ መድቦኛል፡፡ በመሆኑም አመልካች የሰጠኝ የዲሲፕሊን ውሳኔ አግባብ አይደለም ተብሎ ወደ ቀድሞ የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ደረጃ -15 ስራ መደብ ላይ እንዲመልሰኝ እንዲሁም በእግድ ምክንያት ያልተከፈለኝን የሐምሌ እና የነሐሴ ወር 2012 ዓ/ም ደመወዝ ብር 20,300.00 አመልካች እንዲከፈለኝ ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡………..
14759
Documents to download
-
209987(.pdf, 832.43 KB) - 1300 download(s)