እነ ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ማስረሻ እና አቶ ኃ/ማርያም ወዳጆ የመ.ቁ.220108 እነ ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ማስረሻ እና አቶ ኃ/ማርያም ወዳጆ የመ.ቁ.220108 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሶስተኛ ሰበር ችሎት ሐሰተኛ ቃለ-መሐላ አቤቱታ ያቀረቡ ባለጉዳይን በችሎት መድፈር ጥፋተኛ ናቸው በማለት ሐምሌ 27 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት በአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን ቀላል እስራት እንዲቀጡ ወሰነ፡፡ ፍርድ ቤቱ በእስራት እንዲቀጡ የወሰነባቸው አቶ ኃይለማርያም ወዳጆ በደሀ ደንብ መስቀልኛ የሰበር አቤቱታ ለማቅረብ የዳኝነት ለመክፈል ምንም ሀብት እና ንብረት የሌላቸውና በቀበሌ ቤት የሚኖሩ መሆኑን በቃለ-መሐላ በማረጋገጥ አቤቱታቸውን በሀሰተኛ መንገድ በማቅረባቸው ነው፡፡ መልካም ንባብ ………
ኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል እና አቶ ፀጋዬ መለሰ የሰ/መ/ቁጥር 204833 ኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል እና አቶ ፀጋዬ መለሰ የሰ/መ/ቁጥር 204833 ጉዳዩ የስራ ክርክር ሲሆን በተጀመረበት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ ተጠሪ በ08/11/2011 ዓ.ም. ጽፈው ባቀረቡት ክስ በአመልካች ሆቴል ውስጥ በዋና ምግብ አዘጋጅነት የስራ መደብ በወር ብር 85,554 እየተከፈለኝ ስሰራ ቆይቼ ግንቦት 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ በግንቦት 14 ቀን 2011 ዓ.ም. በነበረው የሙስሊሞች ጾም አፍጥር ዝግጅት ላይ ጉድለት አሳይተሀል በሚል ከግንቦት 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ የስራ ውሌን አቋርጧል፡፡ ነገር ግን የፈጸምኩት ጉድለት የለም፡፡ ጉድለት አለ ቢባል እንኳን ያለማስጠንቀቂያ ከስራ የሚያሰናብት ባለመሆኑ ስንብቱ ህገወጥ ነው ተብሎ አመልካች የማስጠንቀቂያ ጊዜ፤ የካሳ እና የስንብት ክፍያ እንዲሁም የአንድ ወር ደመወዝ በድምሩ ብር 705,820 እንዲከፍል ይወሰንልኝ በማለት ዳኝነት ጠይቀዋል፡፡…………..
ወ/ሮ ፀሐይነሽ ወርቁ እነ አቶ አርአያ በዛብህ የሰ/መ/ቁ 211693 ወ/ሮ ፀሐይነሽ ወርቁ እነ አቶ አርአያ በዛብህ የሰ/መ/ቁ 211693 መዝገቡ ከቀጠሮ በፊት ሊቀርብልን የቻለው አመልካች/ቾች 23/11ቀን 2ዐ13 ዓ.ም የሰበር አቤቱታው ታይቶ ውሳኔ እስኪሚያገኝ ጊዜ ድረስ በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ችሎት በመ/ቁ 268732 በ15/11/2ዐ13 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ አፈፃፀሙ ታግዶ እንዲቆይ ይታዘዝልን የሚል አቤቱታ በቃለ መሃላ አስደግፈው አቅርበዋል፡፡……..
እነ አቶ ካሳሁን ዘላለም እና የሰሜን ሸዋ ዞን የገቢዎች ዓቃቤ ሕግ የሰ.መ.ቁ 208826 እነ አቶ ካሳሁን ዘላለም እና የሰሜን ሸዋ ዞን የገቢዎች ዓቃቤ ሕግ የሰ.መ.ቁ 208826 ጉዳዩ ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው፡፡ የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካቾች ላይ በስር ፍርድ ቤት ያቀረባቸው ክሶች ሶስት ሲሆኑ ይዘታቸውም፡- 1ኛ ክስ፡- 1ኛ አመልካች የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 120/1 ድንጋጌን በመተላለፍ በደብረብርሃን ከተማ ቀበሌ 06 ገቢዎች ጽ/ቤት በተጨማሪ እሴት ታክስ ግብር ከፋይነት ተመዝግቦ በሬስቶራንት ንግድ ዘርፍ ተሰማርቶ በመስራት ላይ እንዳለ ሕዳር 08 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 7፡15 ሠዓት ሲሆን በሬስቶራንቱ ውስጥ የምግብ እና የመጠጥ አገልግሎት ለመጠቀም የገቡት አቶ ተክልዬ አስራት እና አቶ ብርቅነርህ ደሳለኝ የተባሉት ግለሰቦች ሁለት ጥብስ፤ ሁለት ቢራ እና ሁለት ድራፍት ከተጠቀሙ በኋላ ለጥብሱ ብር 180፤ ለቢራው ብር 50፤ ለድራፍቱ ብር 24፤ በጠቅላላው ብር 254 / ሁለት መቶ ሀምሳ አራት / ከፍለው ሲወጡ ከሽያጭ መመዝገቢያው መሳሪያ የሚወጣውን ደረሰኝ ቆርጦ መስጠት ሲገባው ደረሰኙን ሳይሰጥ ግብይት የፈጸመ እና ወዲያውኑ እጅ ከፍንጅ የተያዘ በመሆኑ በፈጸመው ያለደረሰኝ ግብይት መፈጸም ወንጀል ተከሷል የሚል ነው፡፡…………
የቤጊ ከተማ አስተዳደር እና አቶ ደጉማ ባያ የሰ/መ/ቁጥር 205786 የቤጊ ከተማ አስተዳደር እና አቶ ደጉማ ባያ የሰ/መ/ቁጥር 205786 የሰበር አቤቱታው የቀረበው የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት መዝገብ ቁጥር 335735 መጋቢት 21ቀን 2013 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ተበሎ እንዲታረም አመልካች በመጠየቁ ነው፡፡ ክርክሩ በተጀመረበት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምዕራብ ወለጋ ዞን ቤጊ ወረዳ ፍ/ቤት ተጠሪ ከሣሽ የቤጊ ከተማ መሬት ልማት ማኔጅምንት ፅ/ቤት ተከሣሽ እንዲሁም አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 40(2) መሰረት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ጣልቃገብ ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል፡፡………..