Tuesday, May 20, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation ሀበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር እና አያት አክሲዮን ማህበር የሰ/መ/ቁጥር 250756 የሰበር አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው አመልካች ሐምሌ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ንግድና ኢንቨስትመንት ምድብ ችሎት በመ/ቁ 03219 በቀን 10/09/2015 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እንዲሁም የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 306130 በቀን 30/10/2015 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሊታረም ይገባል በማለት ስለጠየቁ ነው፡፡ጉዳዩ ውል የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁን ተጠሪ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በአሁን አመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ ነው፡፡የአሁን ተጠሪ ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም በተጻፈ ባቀረበው ክስ አመልካች ከተጠሪ ድርጅት አጠቃላይ 10,800 (አስር ሺህ ሰምንት መቶ) ኩንታል ሲሚንቶ ለመግዛት በመስማማት አመልካች ክፍ ያለ ተጠሪ ፈጽመናል፡፡ተጠሪ በተለያየ ጊዜ 4398 ኩንታል ያቀረበልን ሲሆን ቀሪውን 6402 ኩንታል ሲሚንቶ እንዲያቀርቡልን በተደጋጋሚ የጠየቅን ቢሆንም ተከሣሽ ሲምንቶውን ለማቅረብ ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ስለሆነም አመልካች ክፍያ ተፈጽሞለት ማስረከብ የነበረበትንና ያላቀረበውን 6,402 ኩንታል ሲሚንቶ ለተጠሪ እንዲያስረክብ እንዲሁም ተጠሪ በዚህ ክስምክንያት ያወጣነውን የዳኝነትና ሴሎች ወጪዎችን ኪሳራ ጭምር እንዲከፍለን ይወሰንልን በማለት ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ መልካም ንባብ …. Print 5933 Documents to download 250756(.pdf, 1.06 MB) - 659 download(s)