Tuesday, May 20, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation ሃምሳ አለቃ ሽፈራው ተሰማ እና ወ/ሮ ከበቡሽ ከበደ ገረሮ የሰ/መ/ቁጥር 248461 ጉዳዩ አፈጻጸምን የሚመለከት ነዉ፡፡ ክርክሩ በተጀመረበት በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጋብቻ በፍርድ ቤት ዉሳኔ መፍረሱን ተከትሎ በተሰጠ ዉሳኔ መሠረት እንዲፈጸም ተጠሪ ባቀረበችዉ የአፈፃፀም ክስ አቅርባ ለዚህ ሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነዉ ቤት በሀራጅ እንዲሸጥ ትዕዛዝ ከተሰጠ በኋላ አመልካች የቅድሚያ መብት ይሰጠኝ በማለት ጠይቀዋል፤ አመልካች ለቀረበዉ አቤቱታ በሰጡት መልስ ለአፈፃፀም ምክንያት የሆነዉ ቤት በሀራጅ ለመሸጥ የሚያዳግት፣ ቤቱ መግቢያ እና መዉጫ የሌለዉ እና በእኔ የግል ንብረት ዉስጥ የተከበበ በመሆኑ በሀራጅ ሊሸጥ ስለማይችል የቤቱን ግምት እኔ ስጥቻት ቤቱን እንዳስቀር ይፈቀድልኝ በማለት ተከራክረዋል፡፡ ጉዳዩ የቀረበለት የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የቀረበዉን አቤቱታ ከህጉ ጋር መርምሮ ለአፈፃፀም ምክንያት የሆነዉ ንብረት የግራቀኙ የጋራ ሀብት ስለመሆኑ በመዝገብ ቁጥር 126471 ላይ ዉሳኔ ያረፈበት መሆኑን፣ የጋራ ባለመብት የሆነ ሰዉ ደግሞ በሀራጅ የሚሸጥ ንብረት ላይ የቅድሚያ ግዥ መብት ያለዉ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 443 የተደነገገ በመሆኑ ለተጠሪ የቅድሚያ ግዥ መብት ተፈቅዷል፤ አመልካች ግምት ከፍዬ ንብረት ላስቀር በማለት የጠየቁትን በተመለከተ በግራቀኝ ስምምነት መሰረት የሚፈፀም እንጂ በምርጫ የሚፈፀም እና የሀራጅ ዉጤት ከቀረበ በኃላ የሚታይ መሆኑን ጠቅሶ አቤቱታዉን ዉድቅ በማድረግ ብይን ሰጥቷል፡፡መልካም ንባብ …. Print 4974 Documents to download 248461(.pdf, 833.76 KB) - 556 download(s)