Tuesday, May 20, 2025 / Categories: CASSATION, Cassation ህዳሴ ቴሌኮም አክስዮን ማህበር እና አቶ ዳዊት ጂሬኛ የሰበር መዝገብ ቁጥር - 252106 ጉዳዩ የተጀመረው በምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች ተከሳሽ የአሁን ተጠሪ ከሳሽ የነበሩ ሲሆን ከሳሽ ባቀረቡት ክስ በተከሳሽ መስሪያ ቤት ሲሰሩ በመዝገብ ቁጥር 56212 ተከሰው ከተለያዩ ወጪዎች ጋር ብር 65,160.19 (ስልሳ አምስት ሺህ አንድ መቶ ስልሳ ብር ከአስራ ዘጠኝ ሳንቲም) የተወሰነባቸውና ለዚህም ማስፈፀሚያ እንዲሆን የብር 107,591.38 (አንድ መቶ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ዘጠና አንድ ብር ከሰላሳ ስምንት ሳንቲም) አክስዮን ድርሻቸው ላይ ጨረታ የወጣ ቢሆንም የሚገዛ ሰው በመታጣቱ ካላቸው የአክስዮን ድርሻ ላይ ብር 65,160.19 (ስልሳ አምስት ሺህ አንድ መቶ ስልሳ ብር ከአስራ ዘጠኝ ሳንቲም) ተቀንሶ የተከፈለ ስለሆነ ቀሪው የብር 42,631.19 (አርባ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ሰላሳ አንድ ብር ከአስራ ዘጠኝ ሳንቲም) አክስዮን ድርሻ በገንዘብ እንዲከፈለኝ በማለት ክስ ያቀረቡ ሲሆን ይህም ክስ ለተከሳሽ ደርሶ ተከሳሽ የተሻሻለ መልሳቸውን አቅርበዋል የመልሳቸውም ይዘት ከሳሽ በተከሳሽ ድርጅት ውስጥ የአክስዮን ድርሻ ያላቸው ሲሆን ይህንንም የአክስዮን ድርሻ በንግድ ህጉ መሰረት በየአመቱ በድርሻቸው መጠን መክፈል፣ ለ 3ኛ ወገን ማስተላለፍ እና በጨረታ መሸጥ እንጂ ማህበሩ መክሰሩን አውጆ ባልፈረሰበት ሁኔታ ከሳሽ ያለውን የአክስዮን ድርሻ በገንዘብ ተቀይሮ እንዲከፈላቸው የመጠየቅ መብት የሌላቸው በመሆኑ ክሱ ውድቅ ሊሆን ይገባል በማለት የተሻሻለ መልሳቸውን አቅርበዋል፡፡መልካም ንባብ …. Print 381 Documents to download 252106(.pdf, 827.47 KB) - 49 download(s)