Thursday, December 9, 2021 / Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation ህፃን ሒዳያ አማን መሀመድ እና አመተበል መሃመድ የሰ-መ-ቁ 185175 የሰበር አቤቱታው የቀረበው አመልካች የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 86183 በቀን 17/05/2011 ዓ/ም እንዲሁም የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 2301172 በቀን 19/02/2012 ዓ/ም የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ይታረምልኝ በማለት ስለጠየቁ ነው፡፡ ክርክሩ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተጀመረው የአሁን አመልካች ባቀረቡት አቤቱታ ሲሆን የአሁን ተጠሪ 1ኛ ጣልቃ ገብ ነበሩ፡፡የአመልካች ሞግዚት በቀን 14/06/2010 ዓ/ም ባቀረቡት ማመልከቻ የህፃን ሒዳያ አማን ወላጅ አባት በቀን 21/05/2010 ዓ/ም በሞት የተለዩ ሲሆን የወራሽነት ውሳኔ በማቅረብ የሟች የውርስ ሀብት እንዲጣራ የውርስ አጣሪ እንዲሾም ጠይቀዋል፡፡ፍ/ቤቱም የሟች ውርስ እንዲጣራ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ የአሁን ተጠሪ እና ሰነያ መሀመድ ወደ ክርክሩ ጣልቃ ገብተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ገለልተኛ የውርስ አጣሪ ውርሱን አጣርቶ ሪፖርት እንዲያቀርብ ባዘዘው መሰረት በቀን 26/02/2011 ዓ/ም ሪፖርት ቀርቧል፡፡ ግራቀኙም አስተያየታቸውን አቅርበዋል፡፡በተለይም የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-34360 ኦ.ሮ የሆነውን ተሽከርካሪ በተመለከተ የውርስ አጣሪ ባጣራው መሰረት የቀረበው ማስረጃ ተሽከርካሪው በሟች ስም የሚገኝ ቢሆንም ለ1ኛ ጣልቃገብ /የአሁን ተጠሪ/ተሽከርካው ሟችን ጨምሮ ቤተሰባቸውን እንዲረዳ እንዲሁም ለ1ኛ ጣልቃገብም ሀብት እንዲሆን የተገዛ ተሽከርካሪ እንደሆነና ገንዘቡንም ከአረብ ሀገራት በመሰራት ካገኘሁት ገቢ የተገዛ ነው በማለት ተከራክረዋል፡፡ አመልካች በበኩላቸው ይህን ክደው ተከራክረዋል፡፡........... Previous Article እነ ወ-ሮ ፈይዛ ከማል አወል፣አቶ አብዲ አህመድ መሀመድ እና አቶ ካህሳይ ተስፋዝጊ የሰ-መ-ቁ 184601 Next Article እነ ወ/ሮ ወርቄ ከበደ እና ወ/ሮ ዘነበች ይመር የሰ/መ/ቁ 192028 Print 12516 Documents to download ህፃን ሒዳያ አማን መሀመድ እና አመተበል መሃመድ የሰ-መ-ቁ 185175(.pdf, 507.05 KB) - 954 download(s)