/ Categories: CASSATION, Judgement, 2013, Cassation

ሊቢያ ኦይል ኢትዮጵያ ሊሚትድ እና አቶ ዓሊ መሃመድ ፣ወ-ሮ ዘምዘም፣ ወ-ሮ ፎዚያ መሃመድ የሰ-መ-ቁ. 187065

የሰበር አቤቱታው የቀረበው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የሠጠው ውሳኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል በሚል ነው፡፡ የክርክሩን አመጣጥ ከስር ፍርድ ቤት የመዝገብ ግልባጭ እንደተረዳነው አመልካች የስር ፍርድ ቤት ከሳሽ ሲሆን ተጠሪዎች ተከሳሾች ነበሩ፡፡ አመልካች ያቀረበው ክስ በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በቀድሞ ወረዳ 07 ቀበሌ 34 የቤት ቁጥር 787 ተመዝግቦ የሚገኘው ኦይል ሊቢያ ነዳጅ ማደያ ጣቢያ ያረፈበትን ስፋቱ 1100 ካሬ ሜትር ቦታ ከአመልካች ጋር የተቀላቀለው የቀድሞው አጂፕ ኢትዮጵያ አክሲዮን ማሕበር በወቅቱ የመሬቱ ባለርስት ከነበሩት ከአቶ መሃመድ ሁሴን ጋር ባደረገው የመሬት ኪራይ ውል ከሚያዚያ 07 ቀን 1960 ዓ/ም ጀምሮ ለ30 ዓመታ በመከራየትና በቦታው ላይ በራሱ ወጪ የነዳጅ ማደያ ጣቢያ በመገንባት አገልግሎት ሲሰጥበት ቆይቶ በአዋጅ ቁጥር 47/1967 የመሬት ባለቤትነት ወደ መንግሥት ሲዛወር የኪራይ ውሉ ተቋርጦ ተከራዩ ለመንግሥት የቦታ ኪራይ እየከፈለ የመሬቱ ሕጋዊ ባለይዞታ ሆኖ እንዲጠቀም በሕግ የተረጋገጠ መብት አግኝቷል፡፡ አዋጁን ተከትሎ በወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ መሠረትም የነዳጅ አከፋፋይ ድርጅቶች ይሰሩባቸው የነበሩ ይዞታዎች፣ ዲፖዎች፣ ጽ/ቤቶችና ጣቢያዎች የኩባንያዎቹ ድርጅታዊ አቋም እንደሆኑና ከመንግሥት ጋር ግንኙነታቸው እንዲቀጥል ተደርጓል፡፡……….

Previous Article አቶ ደጉ ናኔቻ እና የጉምሩክ ኮሚሽን የሰ-መ-ቁ 187878
Next Article ኢንፎኔት ኮሌጅ ለ የአቶ መንገሻ ታደሰ ወራሽ ወ/ሪት ፍቅርተ መንገሻ የሠ/መ/ቁጥር 198152
Print
14343